Nov 19, 2025 .
የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም በኢትዮጵያ ቆይታ እያደረጉ ሲሆን በዛሬ ውሏቸውም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀስላሴ፣ የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስትሩ ዶክተር ካሳሁን ጎፌ፣ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት በሁለቱ አገራት ባለው ወዳጅነትና ትብብር እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ መክረዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት አዲስ አበባ ሲገቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


