Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 20, 2025 .

“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የዓለም የጥራት ሳምንት የሃገራችን የጥራት ምሰሶ በሆነው በማራኪው የጥራት መንደር ተከፈተ።

“ጥራት፡ በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የዓለም የጥራት ሳምንት የሃገራችን የጥራት ምሰሶ በሆነው በማራኪው የጥራት መንደር በዛሬው ዕለት ተከፈተ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የዓለም የጥራት ሳምንቱን አስጀምረዋ በደረጉት የመክፈቻ ንግግር የዘንድሮው የጥራት ቀን የሚከበረው የኢፌድሪ መንግስት በጠራ እሳቤ ከምን ጊዜውም በላይ ለጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋለ ንዋይ በመመደብ በአፍሪካ ቀዳሚ በዓለም ተወዳዳሪ የጥራት መንደር ገንብተን ባጠናቀቅንበት ማግስት ነው። ያለጥራት በየትኛውም መስክ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት አይታሰብም ብለዋል።

ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰረጸ የሚሄድ ባህልና የተቋማትን ጠንካራ ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት ከውጭ የሚናስገባቸውንም ሆኑ ወደ ውጭ የምንልካቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች የማይዋዥቅ የጥራት ማስጠበቅ ተግባርን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናልም ብለዋል።

በመሆኑም የሃገራችን የኢኮኖሚ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጥራቱ የተጠበቀና የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላ ምርትና አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ማድረስ ለነገዋ ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን በመገንዘብ በየደረጃው በከፍተኛ ትኩረት እንዲሰሩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

የዓለም የጥራት ሳምንትን የጥራት ማረጋገጫ የተሰጣቸውን ከ150 በላይ ድርጅቶች በማሳተፍ በጥራት መንደር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሕዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም የምከበር ይሆናል።
(የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር )

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia