Nov 29, 2025 .
የታክስ እዳ እምነት ስምምነት ቅፅ(ለአነስተኛ አማራጭ ግብር)

የታክስ እዳ እምነት ስምምነት ቅፅ(ለአነስተኛ አማራጭ ግብር)
ከገቢዎች ሚ/ር ያገኘነውን አንድ ቅፅ እናጋራችሁ። ይህ ቅጽ ከታክስ ከፋይ የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ጋር አብሮ የሚያያዝ ነው፤ አማራጭ አነስተኛ ግብር (2.5 በመቶ) ፤ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395 /2017 አንቀፅ 23 ስር የተደነገገ ቢሆንም ፥ ዝርዝር የአፈፃፀም ደንብና መመሪያ እስካሁን ያልወጣ በመሆኑ ዜሮ ( nill) የሚያሳውቅ ግብር ከፋይ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት በሚጠይቅበት ጊዜ 2.5 ማስከፈል ያልተቻለ በመሆኑ ታክስ ከፋዩ ክሊራንስ ምስክር ወረቀቱ ሲሰጠው አማራጭ አነስተኛ ግብር 2.5 ለወደፊት እንደሚከፍል በመስማማትና ግዴታ በመግባት የግዴታ ቅፁን በመፈረም የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት እንዲሠጠው ይደረጋል።
ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድም ይህንን ቅጽ አያይዘነዋል።

