Dec 01, 2025 .
የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት አሠራርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 855/2014

ታክስ ከፋዮች በያሉበት ት/ጽ/ቤት በታክስ ውሳኔ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉበት ተደራሽነት ያለው፤ በአግባቡ የተደራጀ፤ የተቀላጠፈና ፍትሐዊ የሆነ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቅርብ የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት በማደራጀት የታክስ ከፋዮችን ቅሬታ ለመፍታት የሚያስችል ወጥነት ያለው የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤
ታክስ ከፋዮች የሚያቀርቡትን የግብር ውሳኔ ቅሬታ በወቅቱና በቅርበት ባለ መረጃና ማስረጃ ለመወሰን፤ ተገቢው ውሳኔ ተወስኖ መከፈል ያለበት ታክስ ቶሎ ወደ ገቢ እንዲቀየር ለማስቻል፤
ታክስ ከፋዩ የታክስ ውሳኔ ቅሬታውን የሚያቀርበው በሚኒስቴሩ በሚወስንበት የታክስ መጠን በተዋረድ ተከፍሎ በተለየ ሁኔታ ሳይሆን የሚያቀርበውን ቅሬታ መሠረት በማድረግ ታክስ ከፋዩ ባለበት ቅ/ጽ/ቤት ቅሬታውን በማስተናገድ ፍትሐዊነትን ለማስፈንና በታክስ መጠን ያልተገደበ እኩል ተገልጋይነትን ለማረጋገጥ ተገቢ በመሆኑ፤
የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አጣሪ ጽ/ቤት አሠራርን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 855/2014 መውጣቱ ይታወሳል። (ተያይዟል)
Read the full PDF document
A_Directive_Issued_to_Determine_the_Operation_of_the_Tax_Appeals

