Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 02, 2025 .

ከግብር አሰባሰብና ታክስ ውሳኔ ቅሬታ ያላችሁ

▶️ ከግብር አሰባሰብና ታክስ ውሳኔ ቅሬታ ያላችሁ

ከመጪዉ ሐሙስ ህዳር 25/2018 ጀምሮ ጠዋት ከ 2 ሰአት እስከ 7 ሰአት ድረስ  ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዘን ቅሬታ አመራሩ ተቀብሎ የሚስተናግድ መሆኑን በመረዳት ተጨባጭ ቅሬታ ያላችሁ በከንቲባ ፅ/ቤት  ማቅረብ ትችላላችሁ ።

ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ማንኛዉም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ስር ተዋቅሯል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ስር የተዘረጋዉ የቅሬታ አፈታት ስርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ  በዛ ያልረካ ግብር ከፋይ ከንቲባ ፅ/ቤት ማንኛዉንም አይነት ከገቢ አሰባሰብ ፣ ከሰራተኞች ስነምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋዮች ቅሬታዎችን ለመፍታት ዘወትር ሐሙስ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚደመጥ እና ተጣርቶ ምላሽ የሚሰጥበትን አሰራር ዘርግቷል ።

ሁልጊዜም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚተጋዉ እና ህዝብን አዳምጦ ምላሽ መስጠትን የትኩረት ማእከሉ ያደረገዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከንቲባ ፅ/ቤት በሚስጥር ጥቆማ የሚሰጥበትን ነፃ የጥሪ ማእከል 9977 ፣ የሚስጥር ሳጥንን ጨምሮ  በተጨባጭ ቅሬታዉን በአካል ለበላይ አመራር ማቅረብ የሚችልበትን አሰራር የፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ወደ ተግባር ይገባል ።

ከመጪዉ ሐሙስ ህዳር 25/2018 ጀምሮ ጠዋት ከ 2 ሰአት እስከ 7 ሰአት ድረስ  ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዘን ቅሬታ አመራሩ ተቀብሎ የሚስተናግድ መሆኑን በመረዳት ተጨባጭ ቅሬታ ያላችሁ በከንቲባ ፅ/ቤት  ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የከተማዉ አስተዳደር ያሳዉቃል ።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia