Dec 08, 2025 .
“Global Female Enterpreneurship Empowerment Programm- Ethiopia ወርክሾፕ” መሰጠት ተጀመረ፡፡

የሴቶችን ቢዝነስና ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ “Global Female Enterpreneurship Empowerment Programm- Ethiopia ወርክሾፕ” መሰጠት ተጀመረ፡፡
ፕሮግራሙ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ እና CCECC ኢትዮጵያ ኮንሥትራክሽን PLC ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨሥትመንት ኮሚሽንና ከአዲስ ቻምበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ለአስራ አራት ቀናት የሚቆየው ወርክሾፑ በቢዝነስ ሥትራቴጂያዊ እሣቤ፣ በቢዝነስ ሞዴል እንዲሁም ከቻይና ገበያ ጋር በተያያዘ ያሉ የቢዝነስ እድሎችን የሚዳስስ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ሚኒሥትር ካውንሥለር ሊዩ ሺያጉዋንግ በፕሮግራሙ ላይ የሁለቱ ሃገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው ይህ ወርክሾፕም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሣደግና ዓለም አቀፍ የጾታ እኩልነትን ለማምጣት ያለመ የቻይና አንዱ የስትራቴጂ አካል ነው ብለዋል፡፡
በወርክሾፑ በተለያዩ የቢዝነስ መስኮች ላይ ተሰማሩ ሴት የቢዝነስ ባለቤቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡


