Dec 13, 2025 .
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ ባካሄደው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ወሳኝ በሆኑ ብሔራዊ ደረጃዎች ላይ ሰፊ ውይይትና ምርመራ ካደረገ በኋላ አጽድቋል፡፡

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ለሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ በሆኑ ብሔራዊ ደረጃዎች ላይ ሰፊ ውይይትና ምርመራ ካደረገ በኋላ ማፅደቁን የቦርዱ አባልና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ገለፁ።
ከፀደቁት አስገዳጅ ደረጃዎች መካከልም ሀገራችን በቅርቡ ማምረት የጀመረችው እና ለገበያ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ የምትገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች ደረጃ እንደሚገኝበትም ተገልጿል::
የብሔራዊ ደረጃዎች መፅደቅ የሀገራችን አምራቾችና አገልገሎት ሰጪዎች ወደ ላቀ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን በሀገራችን የሚመረቱ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ላቅ ያለ ድርሻ ይኖረዋል::

