የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ 84 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በ3ኛው የደረጃዎች ቦርድ በማስጸደቅ ወደ ተግባር አስገብቷል ::

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ በቅርቡ ባካሄደው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ለሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ በሆኑ ብሔራዊ ደረጃዎች ላይ ሰፊ ውይይትና ምርመራ ካደረገ በኋላ ማፅደቁ ይታወሳል።
68 አስገዳጅ ደረጃዎችን እና 16 የፍተሻ ዘዴ/ደረጃዎችን በድምሩ 84 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በ3ኛው የደረጃዎች ቦርድ በማስጸደቅ ወደ ተግባር አስገብቷል ::
የጸደቁት ደረጃዎች በሦስት ዘርፎች የተለዩ ሲሆን
1. በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ ፡
ሀ. የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች / Natural Gas Products ብዛታቸው 9 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች ፣ለዚሁ ለፈጥሮ ጋዝ ምርቶች የሚያገለግሉ 11 የፍተሻ ደረጃዎች ጋይድላይን /Test Method standards and guidelines.

2. በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ፡-
ሀ. የተፈጥሮ ጋዝ መሰረተ ልማት ደረጃዎች /Natural gas Infrastructure and Facilities ብዛታቸው 23 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች ፣
ለ. የኃይል ፋክተር ማስተካከያ /power factor corrector ብዛታቸው 7 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች፣ በዚሁ ዘርፍ ስር 5 የፍተሻ ደረጃዎች/ Test Method Standards and guidelines.
ሐ. የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች/ Electrical House hold Appliances የማቀዝቀዣ/ፍሪጅ 1 አዲስ አስገዳጅ ደረጃ
3. በኮንስትራክሽን እና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ፡-
የብረት እና አልሙኒየም/ Steel and Aluminum Structures ብዛታቸው 28 የሆኑ አስገዳጅ ደረጃዎች ናቸው::
ደረጃዎቹ ወቅታዊ የሀገሪቱን ፖሊሲ መነሻ አድርገው የተዘጋጁ እንደሆነ ታውቋል::
በተለይ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚታመነው የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ገበያው በሚገባበት ጊዜ ደረጃዎቹን በመተግበር በተገቢው መንገድ ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ እና ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል::

