Dec 29, 2025 .
ኢትዮጵያ ምርጥ የቡና ዝርያዎቿን በቻይና የማከፋፈያ ማዕከል በዙሁዙው ከተማ ልትጠቀም ነው፡- ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

ኢትዮጵያ ምርጥ የቡና ዝርያዎቿን በቻይና ሰፊ ገበያ ውስጥ ለማሰራጨት የሚያስችላትን ስትራቴጂካዊ የማከፋፈያ ማዕከል በዙሁዙው ከተማ ልትጠቀም መሆኑን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ዛሬ አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ በቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍረንስ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፤ የቡና ኢንዱስትሪው ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆኑን ተናግረዋል።

የቡናው ዘርፍ ለሀገሪቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ 25 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን፣
ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ደግሞ 30 በመቶውን በመሸፈን የኢኮኖሚው ዋነኛ የጀርባ አጥንት እንደሆነም ጠቁመዋል።
በቻይና የሚቋቋመው ማዕከል የኢትዮጵያን ቡና ይበልጥ ተደራሽ ከማድረጉም ባለፈ፣ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ ሰንሰለት ውስጥ ያላትን ተጠቃሚነት ከፍ እንደሚያደርገው ፕሬዚዳንት ታየ ጠቁመዋል።
ቡና የኢትዮጵያ ማንነትና ሕይወት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ የቻይና ዜጎች ይህንን ምርጥ ጣዕም ያለውን የኢትዮጵያ ቡና የሕይወት ዘይቤያቸው አንድ አካል አድርገው እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

