Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 30, 2025 .

በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የተዘጋጀው የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ በኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ ።

ኢንቨስትመንት ፣ መልካም አስተዳደር እና የተቋማት ቅልጥፍና ለግሉ ዘርፍ ልማት በኢትዮጵያ በሚል በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የተዘጋጀው የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ በኢሊሊ ሆቴል ተካሄደ ።

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ መብት፤ፍላጎትና ጥቅምን የሚያስጠብቅና በሀገሪቱ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን ሚና የሚወጣ የግሉ ዘርፍ ድምጽ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ምክር ቤቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ምህዳር እንዲሻሻልና አባላቱ የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ሃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች መካከል አንዱ በተለያዩ ሀገራዊና የንግድ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ምክክር በማድረግ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ጥረት ማድረግ ነው ::

የዚሁ አንድ አካል የሆነው የመንግስተና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ  ‘ኢንቨስትመንት፤ መልካም አስተዳደርና የተቋማት ቅልጥፍና ለግሉ ዘርፍ ልማት ’ በሚል የፓናል ውይይትና የጋራ የምክክር መድረክ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሂዷል፡፡

የምክክር መድረኩ ኢንቨስትመንት፤ የመልካም አስተዳደርና የተቋማት ቅልጥፍና ለግሉ ዘርፍ ያላቸው ትስስር እና ሚና እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ነክ ጉዳዮች ላይ የንግዱ ህብረተሰብና መንግስት ተቀራርበው እንዲሰሩ ከማድረጉም በላይ ችግሮች ስር ሳይሰዱ ቶሎ የመቅረፍ እድሉን በማግኘት መፍትሄዎቹንም በጋራ ለማፈላለግ ጠቃሚ እንደሆነ የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ መድረኩን ሲከፍቱ ተናግረዋል ፡፡

አዲስ ቻምበር ከአለም አቀፉ የግል ኢንተርፕራይዝ ማእከል ጋር ባዘጋጀው መድረክ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ገቢዎች እና ኢንቨስትመንት ቢሮዎች ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከግሉ ዘርፍ የተወከሉ የተለያዩ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል ።

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በእድገት ፍጥነት ረገድ ተጠቃሽ እየሆነ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን እየታዩ ያሉ የመልካም አስተዳደርና የተቋማት ቅልጥፍና ወይም የቅንጅት ክፍተቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ስራና ዘላቂነት ላይ ተግዳሮት መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

በተለይ በሀገሪቱ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የንግዱ ህብረተሰብ አባላት ሚና የሚወጡት መልካም አስተዳደር በየተቋማቱ ሲሰፍንና አሰራሮች ሲዘምኑ መሆኑን በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የተቋማት መዳከምና ብቃት አለመኖር ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር ተዳምሮ የሀገርን ኢኮኖሚንና ኢንቨስትመንትን እየጎዱ እንደሚሄዱ የንግዱ ህብረተሰብ በመድረኩ ላይ ሀሳቡን አንፀባርቋል ፡፡

የኢንቨስትመንት ዘላቂነት ሊኖር የሚችለው በየአካባቢው ያለው የሀገራችን የተቋማት ጥንካሬ ሲገነባና የመልካም አስተዳደር ሁኔታዎች በአስተማማኝ መልኩ ሲረጋገጡና በቅልጥፍና እና በቅንጅት ሲሰሩ እንደሆነ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ ተናግረዋል ፡ ፡

የግሉ ዘርፍም ቢሆን ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ የሞራል እሴቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት ብለዋል ፡፡

ከስነምግባር ውጪ ሆኖ በአጭሩ በሙስና ለመክበር መሞከር ግን ራስን እንደማጥፋት፤ በትውልድም እንደመደራደር መሆኑን አሳስበዋል።

የግሉ ዘርፍ ራሱ ሥነምግባርን የተላበሰ አሠራርን የሚያበረታታ አጥፊዎችን ግን በራሱ የሚኮንንና የሚያስተምር መሆን ይገባዋል ብለዋል ፡፡

በአጠቃላይ መድረኩ ሁሉም ተቋማት ኢንቨስትመንትን እና ዘላቂ ልማትን ከሚገቱ፤ ውድድርን ከሚያደናቅፉ እንቅፋቶች ማለትም ከሙስና፤ከብልሹ አሰራርና ከኢስነምግባራዊ ድርጊቶች በመታቀብ የሀገራችንን ግል ዘርፍ መፃኢ እድል የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ከ 150 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው የግልና የመንግሥት ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።

አዲስ ቻምበር ባለፉት 3 ወራት ብቻ በታክስ ፤ በጉምሩክ፤ በሰላምና ንግድ ዙሪያ ያተኮሩ ታላላቅ የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ የአድቮኬሲ የምክክር መድረክ አካሂዷል ።

በቀጣይም አዲስ ቻምበር በፋይናንስ ፣በመስሪያ ቦታና በውጭ ምንዛሬ አቅራቦት ዙሪያ የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ ምክክር እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል ።
(የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia