Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 12, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የኢትዮ- አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ልዑካን በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የኢትዮ- አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ልዑካን በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ምክር ቤቶቹ በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች በትብብር ለመስራት ነው በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና መስሪያ ቤት የተወያዩት፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ፣ የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ኤልያስ ወልዱ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እንዲሁም የሁለቱ ምክር ቤቶች የቦርድ አባላትና የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

  

ዶክተር ዓይናለም አባይነህም በምክር ቤቱ በኩል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንና የምክር ቤቱን ሀገራዊ ተልዕኮዎች በማንሳት በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፣ በአድቮኬሲና ምርምር እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ በመሆን ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ የምክር ቤቱን ዓላማዎች እንዲሁም ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች ለልዑካኑ ያቀረቡ ሲሆን ሁለቱ የንግድ ምክር ቤቶችም በሁለቱ ሀገራት ያለውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ በሚቻልባቸው አግባቦች ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡

የኢትዮ- አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ ኤልያስ ወልዱ በበኩላቸው በሁለቱ ምክር ቤቶች መካከል በተለዩ እና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያሳድጉ የኢኮኖሚ ዘርፎች በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ኤልያስ ውጤት ሊያመጡ በሚችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቢዝነሶች የአሜሪካን ገበያ መጠቀም በሚቻልባቸው መንገዶች በትብብር መስራት እንደሚገባም የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡

የኢትዮ- አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ዙሪያም ጉብኝቶችን ለማካሄድና ሲምፖዚየም ለማዘጋጀት በሂደት ላይ መሆኑም ተገልጧል፡፡

በፕሮጀክት የታገዙ ስራዎችን መስራት፣ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረምና የጋራ የቢዝነስ ካውንስል በማቋቋም ጠንካራ ትስስር ለመፍጠር እንደሚሰራም በፕሮግራሙ ላይ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮ- አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላትም ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓም በአዲስ አበባ በሚካሄደው 15ኛው ኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ላይ እንዲሳተፉ በምክር ቤቱ በኩል ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia