Jan 26, 2026 .
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ፕሬዚዳንት ክቡር ሰብስብ አባፍራ አባጆቢር የተመራዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑካን ቡድን ለስራ ጉብኝት አዋሳ ገብቷል።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ፕሬዚዳንት ክቡር ሰብስብ አባፍራ አባጆቢር የተመራዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ለማድረግና ከሲዳማ ክልል የመንግስት አካላት ጋር የንግድ ምክር ቤቶችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር አዋሳ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አዋሳ አዉሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት መኩርያ፣ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ቡርቃ ቡጡላ፣በሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባት፣ በሲዳማ ክልል ንግዶና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳን አቶ ዘሪሁን ቃሚሶና በዋና ፀሐፊዉ አቶ ደመቀ ደፋሮ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

