Jan 26, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር- የእንኳን ደስ ያሎት ዝግጅት

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላት እና አመራሮች በቅርቡ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የከፍተኛ ግብር ከፋይ የወርቅ ሽልማት እና እውቅና ላገኙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የእንኳን ደስ ያሎት ዝግጅት አካሄዱ::
የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት አመት የግብር እና ታክስ አፈፃፀም ረገድ ግዴታቸውን በታማኝነት ለተወጡ ለክልሉ ግብር ከፋዮች በቅርቡ እውቅናና ሽልማት ማበርከቱ ይታወሳል።


