Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 29, 2026 .

አቶ  ሰብስብ አባፊራ አበጆቢር  የኢትዮጵያውያን አንድነት መገለጫ የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ  ፎቶ ግራፍ ለሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በስጦታ አበርክተዋል፡፡

  

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ  ሰብስብ አባፊራ አበጆቢር  የኢትዮጵያውያን አንድነት መገለጫ የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ  ፎቶ ግራፍ ለሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩርያ በኩል እንዲደርሳቸው በስጦታ አበርክተዋል፡፡

ስጦታውን በባረከቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክትም  መንግስትና የግሉ ዘርፍ ተቀናጅቶ  በመስራት  የአገር ኩራት የሆነውን ታላቅ ፕሮጀክት ዕውን በማድረግ የጋራ አሻራቸውን እንዳሰረፉ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ጉልህ አሰተዋፅኦ እያበረከተ  ያለውን የግሉን ዘርፍ  በማጠናከር  ተገቢውን ሚና እንዲጫወት የግሉ ዘርፍ ድምፅ የሆኑና በየደረጃው ያሉ የንግድ ምክር ቤቶችን ለማጠናከርም በቅንጅት እንስራ ብለዋል፡፡

በሲዳማ ክልል የሚገኙ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች እንዲጠናከሩ ደግሞ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት መዋቅር ተገቢውን ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልፀው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ለምክር ቤቶቹ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው አቅጣጫ እንዲሰጡም  በንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዋ በኩል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመርሐ ግብሩም ላይ በሲዳማ ብሔር ባህል ለክብር እንግዳ የሚቀርበው ሻፌታ የተባላ የክብር የባህልና የአንድነት መገለጫ የሆነዉን የጋራ መሶብ በአቶ ሰብስብ አባፊራ ለተመራው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ቀርቧል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia