የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባለድርሻ አካላትን ያካተተ 4ኛዉን አገር አቀፍ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤ በስካይላይት ሆቴል


የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባለድርሻ አካላትን ያካተተ 4ኛዉን አገር አቀፍ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤ በስካይላይት ኢትዮጵያ ሆቴል እያካሄደ ነዉ።
ገባኤዉን በንግግር የከፈተቱት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አይናለም አባይነህ ህገ ወጥ ንግድ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ከማሳደሩም በላይ የብሔራዊ ደህንነት ስጋትም ነዉ ብለዋል። ህገ ወጥ ንግድ ህጋዊ ነጋዴዎች ከዉድድር ዉጭ የሚያደርግ እንደመሆኑ መጠን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግሉ ዘርፍ ድምፅ እንደመሆኑ መጠን ህገ ወጥ ንግድን ለማስቆም ከሚመለከታቸዉ የመንግስት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።


የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸዉ ህገ ወጥ ንግዶ በሚያደርሰዉ ጉዳት ዙርያ በመረጃ የተደገፉና በጥናት የተረጋገጡትን ባለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት በተካሄዱት የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤዎች ላይ ሰፊ ግንዛቤ መፈጠሩን አንስተዉ የዚህ የ4ኛዉ ጉባኤ ዓላማ ግን በተቀናጀ መልኩ ወደ ተግባር ለመግባት ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት መሆኑን አስረድተዋል።
ያለፉት ሶስት አገር አቀፍ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤዎች ጥቅል ሪፖርትና የጥናት ግኝቶች እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ ቀርቧል።

