Mar 28, 2026 .
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ይገኛል።



የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል “በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ ” በሚል መሪ ቃል በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ይገኛል።
ክብረ በዓሉ ከመጋቢት 19-22/2018 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች ይከበራል፡፡ በዚህ ታሪካዊ ክብረ- በዓል ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሰብስብ አባፊራን ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት በድምቀት በአድዋ ድል መታሰቢያ በመከበር ላይ ይገኛል።


