Mar 28, 2026 .
ንግድ ሳይንስ በሆነበት ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት በእውቀት መምራት ያስፈልጋል:- ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ


ንግድ ሳይንስ በሆነበት ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት የንግድ ክህሎትን ማሳደግና በእውቀት መምራት ያስፈልጋል ሲሉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ገለፁ ።
ይህንን የተናገሩት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለንግድ ምክር ቤቶች ዋና ፀሐፊዎች በ”Chambers leadership and Governance “በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል የአቅም መጎልበቻ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ነው ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከተልዕኮዎቹ አንዱ የአባላትን አቅም መገንባት መሆኑን ገልጸው ዋና ፀሐፊዎችም “የሊደርሽፕና ገቨርናንስ” እውቀትና ክህሎታቸውን በማሳደግ የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጣና መቀላቀሏን እንዲሁም የአለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል በሂደት ላይ መሆኗ ለንግዱ ማህበረሰብ መልካም አጋጣሚ ነዉ: ይሁን እንጂ መጪው ጊዜ ውድድር የሚጠይቅ በመሆኑ መዘጋጀትን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የንግድ ምክር ቤቶች ኃላፊዎችም ንግድ እንዲዘምን ፣ ሳይንሳዊ እንዲሆን መስራት እንዳለባቸው አሳሰበው አጠቃላይ የንግድ ኮሙኒኬሽን ስርዓቱን የሚፈትሹና የሚያዘምኑ ፣ ራሳቸውን የሚያበቁ መሆን እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

