የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለክልልና ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ዋና ፀሐፊዎች ስልጠና ሰጠ።



የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለክልልና ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ዋና ፀሐፊዎች ስልጠና እየሰጠ ነው።
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት. በ”chamber leadership and Governance” ከተለያዩ የክልልና ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ለተወጣጡ ዋና ፀሐፊዎች እና ለምክር ቤቱ የማኔጅመንት አባላት በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ነው።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች አቅማቸውን የሚያሳድጉ ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎች ማግኘት አለባቸው ብለዋል ።
አክለውም የግሉ ዘርፍ የሚገጥሙትን የተለያዩ ተግዳሮቶች ለመፍታት ስልጠናዎችን መውስድና መፍትሄ ማበጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
የምክር ቤቱ የአባላት ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ እሱባለው ተስፋ በበኩላቸው የሚሰጡ የአቅም መጎልበቻ ስልጠናዎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን ገልጸው ፣ ስልጣኞች የሚገኙ እድሎችን መጠቀም እንደሚገባ አሳሰበዋል ።

ECCSA Provides Training on Chamber Leadership and Governance
The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) has launched a capacity-building training program for representatives drawn from regional chambers, focusing on chamber leadership and governance.
Opening the training, Deputy Secretary General Mrs. Helen Retta emphasized the critical importance of continuous capacity-building initiatives to strengthen the private sector. She noted that such trainings play a key role in addressing the persistent challenges faced by businesses and in enhancing the effectiveness of chambers in advocating for their members.
Mrs. Helen highlighted that empowering chamber leaders with the necessary knowledge and skills will contribute to improving service delivery, promoting good governance, and fostering a more enabling business environment.
On his part, Director of the Member Affairs Directorate, Mr. Esubalew Tesfa, urged participants to make the most of the opportunity. He encouraged trainees to follow the sessions attentively and actively engage throughout the training program to gain practical insights that can be applied in their respective regional chambers.
The training is expected to enhance leadership capacity, strengthen governance structures, and improve coordination among chambers across the country.

