ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በኢትዮጵያ ከኮሎምቢያ አምባሳደር የሰን አርካዲዮ ጋር ተወያዩ፡፡






ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በኢትዮጵያ ከኮሎምቢያ አምባሳደር የሰን አርካዲዮ ጋር ተወያዩ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከአምባሳደር የሰን አርካዲዮ ሜኔሴስ ኮፔቴ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማሻሻል የሚቻሉ እድሎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ኮሎምቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ አምባሳደር የሲን አርካዲዮ ገልጸዋል።
አምባሳደር አርካዲዮ ኮሎምቢያ በአፍሪካ ያላትን የንግድ ተሳትፎ ለማስፋት እንደምትፈልግ ገልጸው በተለይም በኢትዮጵያ በኩል ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትሻ ነው የገለጹት፡፡
ዶ/ር ቀነኒሳ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ስላለው አስተማማኝ የንግድና የኢንቨስትመንት ሁኔታ ገልጸውላቸዋል። በአገሪቱ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ የተመረጡና እንደ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን እና ሌሎች ዘርፎች ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍትና አስተማማኝ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ሁለቱ አገራት በአግሮ-ቴክኖሎጂ፣ በታዳሽ ኃይል፣ ማዕድን እና አግሮ-ኬሚካል ዘርፎች በጋራ ለመስራትና የንግድ ለውውጥ ለማካሄድ እንደሚችሉ ተብራርቷል፡፡
የዲፕሎማሲ ትብብርን ለማጠናከር፣ የንግድን ልውውጥን ለማበረታታት እና የባህል ግንኙነቶችን ለማሳደግ በማለም ኮሎምቢያ ባለፈው ነሐሴ/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን እንደገና መክፈቷ ይታወሳል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷንና ያላትን ስትራቴጂካዊ ሚና የሚያመላክት ነው።
Colombia is seeking to strengthen its business and economic ties with Ethiopia, according to the Colombian Ambassador to Ethiopia, Yeison Arcadio.
The Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, Dr. Kenenisa Lemie (Associate professor), met with Ambassador Arcadio to discuss opportunities for enhancing trade and investment relations between the two countries.
Deputy Secretary General, Ms. Helen Reta, along with other management members, was also in attendance.
During the discussion, Dr. Kenenisa highlighted Ethiopia’s favorable trade and investment climate.
He noted that priority sectors under the country’s homegrown economic reform agenda such as agriculture, manufacturing, mining, and others—are open and attractive to foreign investors.

Ambassador Arcadio stated that Colombia is keen to expand its business engagement across Africa, with a particular focus on Ethiopia.
He emphasized that both countries can collaborate and exchange products in key sectors including agro-technology, clean energy, mining, and agro-chemicals.
Colombia officially reopened its embassy in Addis Ababa in August 2025 to strengthen diplomatic cooperation, promote trade, and enhance cultural ties, recognizing Ethiopia’s strategic role as a diplomatic hub in Africa.

