Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 01, 2026 .

የናይጄሪያ “Motherland Beckons – IPADA ኢንሼቲቭ” ልዑካን ቡድን ከዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ተወያየ።

የናይጄሪያ “Motherland Beckons – IPADA ኢንሼቲቭ” ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ተወያየ።

IPADA ኢንቬቲቭ በአፍሪካ መንግሥታትና በግል ዘርፍ መካከል  ስትራቴጂያዊ ድልድይ በመሆን የሚሠራ ሲሆን በውስጣዊ የአፍሪካ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም እና የዲያስፖራ ተሳትፎና ትስስር ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ተቋም ነው።

የድርጅቱ መስራች ኦቱንባ ዋንሌ አኪንቦቦዬ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በጉዞ እና በኪነ-ጥበብ ሥራዎች የአፍሪካን አንድነት ለማጠናከር የሚያስችል ራዕይ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የ“Motherland Beckons” ኢንቬቲቭ ዋና መስሪያ ቤት መቀመጫነት  መመረጧን ገልጸው፣ ይህም በምስራቅና በምዕራብ አፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት በቱሪዝምና በባህል ልውውጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልጸዋል።

እስከ 2030 ድረስ የአፍሪካ ዘር ያላቸው 100 ሚሊዮን የዲያስፖራ ማህበረሠብ አባላት ወደ አፍሪካ እንዲመጡ ለማበረታታት እቅድ ተይዟልም ብለዋል።

በ“Invest in Ethiopia ጉባኤ” ላይ መሳተፍ እንዲሁም 100 ሚሊዮን ዛፎችን በመላው አፍሪካ መትከል ያሉ ፕሮግራሞች ከተያዙ እቅዶች መካከል የተካተቱ ናቸው።

ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ንግድና በኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አብራርተው ከIPADA ኢንቬቲቭ ጋር በመተባበር የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደትና አንድነት ለማጠናከርና በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የIPADA ኢንሼቲቭ ከናይጀሪያ የንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድንና ግብርና ምክር ቤት ጋር በመሆንና በማስተባበር  የናይጄሪያ የንግዱ ማህበረሠብ ተወካዮች በ“Invest in Ethiopia ጉባኤ” ላይ እንዲሳተፉ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

የናይጀሪያ የንግድ፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድንና ግብርና ምክር ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫእ  የመክፈት እቅድ እንዳለውም ተጠቁሟል።
በውይይቱም የናይጀሪያ ሴናተር ባባፌሚ ኦጁዱ እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ ተገኝተዋል።

A delegation from the Nigerian Motherland Beckons – IPADA Initiative held a high-level meeting with Dr. Kenenisa Lemie, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA).

The IPADA Initiative aims to serve as a strategic bridge between African governments and the private sector, with a strong focus on enhancing intra-African trade, investment, tourism, and diaspora engagement.

During the meeting, Otunba Wanle Akinboboye, Founder of the initiative, outlined its vision of fostering African unity through trade, investment, travel, and the arts. He emphasized that Ethiopia has been selected as the headquarters for the Motherland Beckons initiative designed to strengthen ties between East and West Africa through tourism and cultural exchange.

Mr. Akinboboye also highlighted an ambitious goal to encourage 100 million people of African descent in the diaspora to visit Africa by 2030. As part of this vision, the initiative has developed a five-year schedule that includes participation in key continental events such as the Invest in Ethiopia Summit, as well as environmental efforts like planting 100 million trees across Africa.

Dr. Kenenisa Lemie reaffirmed ECCSA’s commitment to promoting trade and investment. He expressed the Chamber’s strong interest in partnering with the IPADA Initiative to advance Africa’s economic integration.

The meeting also noted that representatives from IPADA and Nigerian businesses participated in the Invest in Ethiopia Summit in collaboration with the Nigerian Association of Chambers of Commerce Industry Mines and Agriculture (NACCIMA), which is planning to establish an operational presence in Ethiopia.

Other notable attendees included Helen Reta, Deputy Secretary General of ECCSA, and Babafemi Ojudu, Nigerian Senator.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia