የምክር ቤታችን አዲሱ ገፅታ የረዥሙ ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ ምልክት:- ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የምክር ቤታችን አዲሱ ገፅታ የረዥሙ ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ ምልክት፣ የግሉ ዘርፍ የብርታት እና የዕድገት ራዕይ፣ የአመራር ውጤታማነት ብሎም የግሉ ዘርፉ በኢኮኖሚያዊ ልማት ውስጥ ላለው ዘላቂና የአይተኬነት ሚና ምስክር ነው።
በአዲስ መልክ የታደሰው እንዲሁም የአካባቢውን ገፅታ በሚለውጥ መልኩ የታችኛው ወለል ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የገበያ ማዕከል ሆኖ የተሻሻለው የምክር ቤቱ ባለ ሰባት ወለል ሕንፃ የተቋሙን የረጅም ዓመታት የተፅዕኖ ፈጣሪነት ጉዞ ወደ ወሳኝ ደረጃ ያሸጋግረዋል።
እንደሚታወቀው ምክር ቤታችን ከ75 ዓመታት በላይ የአገራችን የግሉ ዘርፍ አምድ ሆኖ ዘልቋል። የገበያ ማዕከሉን ጨምሮ አዲሱ የሕንፃ ገፅታ ለውጡም ከአዲስ አበባ የከተማ ማስዋብና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ጋር እንዲጣጣም ሆኖ የተከናወነ ከመሆኑ አንፃር የግሉ ዘርፍ ትልቅ ምልክት ነው።
ይህም፤ ምክር ቤታችን የግሉ ዘርፍ ከአገራዊ የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ባሻገር በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ሚና ያለው ተዋናይ እንዲሆን ለሚያከናውነው ተግባር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።
የምክር ቤታችንን የአሰራር እና የገፅታ መዘመን የምንፈልገው ለስነ-ውበት ካለን ፍቅር ብቻ ሳይሆን ለውጡ ለሌላኛው ትልቅና ማሳካት ለምንፈልገው የግሉ ዘርፍ ቁልፍ ሚና ውጤታማነት ግብዓት ጭምርም በመሆኑ ነው።
ከዚህ አንፃር፤ በቅርብ ጊዜያት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትም ምክር ቤታችንን የንግድና ኢንቨስትመንት ዲፕሎማሲ ማዕከል ፣ የውይይት፣ የትብብርና የንግድ ማከናወኛ መድረክ በማድረግ ወደ አዲስ ምዕራፍ የማሸጋገር ጅማሯችን ማሳያ ነው።
በሕንፃው እንደ አዲስ የተደራጀው የንግድ ማዕከልም የምክር ቤቱን የውስጥ አቅም ብቻ ለማሻሻል ተብሎ የተሰራ ሳይሆን ከአካባቢው ውበት ጋር ተዋሕዶ የከተማይቱን የንግድና ዲፕሎማሲ ማዕከልነት ለማጠናከርም ጭምር ነው።
በአጠቃላይ የምክር ቤታችን አዲሱ ገፅታ የረዥሙ ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ ምልክት፣ የግሉ ዘርፍ የብርታት እና የዕድገት ራዕይ፣ የአመራር ውጤታማነት ብሎም የግሉ ዘርፉ በኢኮኖሚያዊ ልማት ውስጥ ላለው ዘላቂና የአይተኬነት ሚና ምስክር ነው።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት





The inauguration of the newly renovated headquarters of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations marks a defining moment in the institution’s long and impactful journey.
For more than 75 years, the Chamber has stood as a pillar of Ethiopia’s private sector development. Today, its renewed presence reflects both continuity and transformation, honoring its legacy while embracing a modern vision.
The new building presents a fresh and confident face, aligned with the evolving character of Addis Ababa. Designed to complement the city’s beautification initiatives and urban renewal efforts, it stands as a symbol of progress and ambition. Its architectural renewal is not only aesthetic but also purposeful, positioning the Chamber as a dynamic hub for business engagement and policy dialogue.
Strategically, the building aspires to serve beyond national boundaries. It is envisioned as a center for African business diplomacy, fostering stronger connections across the continent.
By providing a platform for dialogue, partnerships, and trade facilitation, it reinforces Ethiopia’s role within the broader African economic landscape.
The transformation of the Chamber’s headquarters has been made possible through the vision and commitment of its Board.
Their leadership in guiding the renewal process reflects a clear understanding of the institution’s future direction. By prioritizing modernization while safeguarding institutional values, the Board has ensured that the Chamber remains relevant, responsive, and forward looking.
As a center of business, the new building not only enhances operational capacity but also enriches its surroundings. It integrates seamlessly with its environment, contributing to the city’s growing stature as a commercial and diplomatic hub.
Ultimately, the renewed Chamber stands as a testament to resilience, leadership, and the enduring role of the private sector in shaping Ethiopia’s economic future.

