የቁርስ ውይይት ስለ ክህሎቶች እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ጥምረት

የቁርስ ውይይት ስለ ክህሎቶች እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ጥምረት
የኢትዮጵያን የሰራተኛ ገበያ በማመጣጠን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የተካሄደ የምክክር መድረክ
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የግሉን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማጎልበት እና ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ጋር የተያያዘ የሰው ኃይል ክህሎት ልማትን ለማጠናከር ያተኮረ የቁርስ ውይይት እና የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል።
በመድረኩ ላይ ከአገር ውስጥና ከውጭ የግሉን ዘርፍ የሚወክሉ ተቋማት ተሳትፈዋል። ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (ECCSA)፣ አዲስ ቻምበር፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት እና ሌሎች አጋር ተቋማት ተገኝተዋል። ከመንግስት በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የሳይንስ እና ኢኖቬሽን ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የፌደራል ተቋማት ተሳትፈዋል።
በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ ያላትን ምቹ የኢንቨስትመንት አየር እና የውጭ ባለሀብቶች የሚያሳዩትን ከፍተኛ ፍላጎት በመጠቀም ከዓለም አቀፍ የስራ ገበያ ጋር ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት የመንግስት፣ የኢንዱስትሪዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲዎች ቅንጅት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ በስፋት ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ፍቅሬ፣ ምክር ቤቱ በ“ቻምበር አካዳሚ” አማካኝነት በቴክኒክ፣ በሙያ እና በሌሎች ተያያዥ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የግሉን የንግድ ማህበረሰብ አቅም ለማጎልበት እያከናወነ ያለውን ሰፊ ስራ አብራርተዋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ከGIZ፣ ከተለያዩ የውጭ የልማት አጋሮች እና ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ጥረት እና ከንግድና ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ጋር የጀመረውን ትስስር ለማጠናከር ያለውን የወደፊት ቁርጠኝነት በስፋት ገልጸዋል።

Breakfast Dialogue on Skills and FDI Synergy
Consultative Forum on Aligning Ethiopia’s Labor Market to Enhance Foreign Direct Investment (FDI)
The Ministry of Labor and Skills organized a high-level breakfast dialogue and consultative forum focused on strengthening workforce development and enhancing the competitiveness of Ethiopia’s private sector in alignment with Foreign Direct Investment (FDI) opportunities.
The forum brought together representatives of both local and international private sector institutions, including the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), Addis Chamber, the U.S. Embassy in Ethiopia, the American Chamber of Commerce and other development partners. Government institutions such as the Ethiopian Investment Commission, science and innovation institutions and other invited federal agencies also participated in the discussion.
During the forum, participants emphasized the importance of building a skilled and globally competitive workforce that matches Ethiopia’s favorable investment climate and the growing interest of foreign investors. Strong collaboration among government institutions, industries, Technical and Vocational Education and Training (TVET) institutions, and universities was highlighted as essential to achieving this objective.
Mr. Wasihun Fikre, Head of the President’s Office at the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), stated that the Chamber, through its “Chamber Academy,” is actively working to strengthen the capacity of the private business community through technical, vocational and other comprehensive capacity-building training programs.
He further explained ECCSA’s ongoing collaboration with GIZ, international development partners, and relevant government institutions to develop a competent and competitive workforce. He also highlighted the Chamber’s commitment to strengthening its partnership with the trade and manufacturing sectors and expanding future collaborative initiatives.

