በ3ኛው አገራዊ የቢዝነስ አጀንዳ የተገኙ ውጤቶችን በፍጥነት ወደስራ ማስገባት ይገባናል:- ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት 3 ኛውን ብሔራዊ የቢዝነስ አጀንዳ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ዛሬ አካሂዷል።
በኢትዮጵያ የተሻሻለና ቀልጣፋ የኢኮኖሚ ስርዓት በመዘርጋት ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ጊዜ ሳይሰጡ የመፍታት፣ የመመካከር ባህልን የማስፋት ፣ አሳታፊነት እና አካታች አሰራሮችን ማሳደግ… ወዘተ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው።
ከዚህ አንፃር መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየወሰዳቸው ያሉ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማጠናከር ስራዎች፤ ለንግድና ኢንቨስትመንት አመቺ ሁኔታን የሚፈጥሩ የመሰረተ ልማት የማጠናከር ተግባራት የአሰራሮች ቅልጥፍናን በማሻሻል እንዲሁም የንግድ ምህዳሩን ቀልጣፋና አመቺ በማድረግ ረገድ ሚናቸው ላቅ ያለ ነው።
በመሆኑም በዚህ ፈጣን የለውጥ ሂደት ውስጥ የግሉ ዘርፍ የሚያከናውናቸው ስራዎችም በዚያው መልኩ ሊሆን ይገባል።
ከዚህም በተጨማሪም፤ በቅርብ ጊዜ እንደጀመርነው በሕግ አውጪው የመንግስት አካላት በሚደረጉ የሕግ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ በቂ ዝግጅት በማድረግ ተሳትፎን ማጠናከር በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ለምናከናውነው ስራችን አጋዥ ይሆናሉ።
እንዲሁም ከ3ኛው አገራዊ የቢዝነስ አጀንዳ ዝግጅት ባሻገር ፤ በየደረጃው ካሉ አባል ምክር ቤቶቻችን ጋር በመሆን የንግዱ ማኅበረሰብ የአስተያየት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት ይኖርብናል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ፤ ዛሬ ያከናወነው 3ኛው አገራዊ የቢዝነስ አጀንዳ የተገኙ ውጤቶችን በፍጥነት ወደስራ ማስገባት ይገባናል።
በመጨረሻም፤ በዚህ መድረክ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
ECCSA today conducted the 3rd National Business Agenda Validation and Consultation Forum.
Establishing an improved and efficient economic system in Ethiopia and ensuring sustainable growth require the timely resolution of challenges faced by the private sector, the promotion of a culture of consultation, and the strengthening of participatory and inclusive approaches. These are among the critical issues that deserve attention.
In this regard, the economic structural reforms recently undertaken by the government, efforts to strengthen public service delivery, and initiatives aimed at improving infrastructure that supports trade and investment play a significant role in enhancing operational efficiency and creating a more conducive and competitive business environment.
Accordingly, within this rapid process of change, the activities and contributions of the private sector should also progress at the same pace.Furthermore, as we have recently begun doing, strengthening participation in legislative consultation forums organized by government bodies through adequate preparation will greatly support our efforts in the areas of trade and investment.
In addition, beyond the preparation of the 3rd National Business Agenda, we need to work closely with our member chambers at all levels to organize consultation and dialogue forums that gather the views and concerns of the business community.
In this connection, the outcomes generated through today’s 3rd National Business Agenda process should be translated into action without delay.
Finally, I would like to express my sincere appreciation to all participants who took part in this forum.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

