ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ The Ethiopian Conflict Sensitivity Hub(ECSH) እና International Finance Corporation (IFC) ጋር ውይይት

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለግሉ ዘርፍ ምቹ የቢዝነስ ከባቢን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከልማት አጋሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ The Ethiopian Conflict Sensitivity Hub(ECSH) እና International Finance Corporation (IFC) ከተባሉ የልማት አጋሮች ጋር ባደረጉት ውይይት የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲጫወትና የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መኖር እንዳለበት በመግለፅ፤ ይህንን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም የግሉ ዘርፍ ድምፅና በግሉ ዘርፍና በመንግስት መካከል አገናኝ ድልድይ የሆነው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡
The Ethiopian Conflict Sensitivity Hub (ECSH) ሰላም የሁሉም መሰረት መሆኑን በመረዳት በተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ለሰላም ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው በሚል መርህ ለግጭትና የሰላም እጦት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን አስቀድሞ በመገንዘብ ለሰላም ግንባታ በሚያግዙ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው፡፡ ከሰላም ግንባታ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤትም ቢዝነስ ለሰላም የሚል ኢኒሽየቲቭ በመቅረፅ ከሰላም ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የግሉ ዘርፍ ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የሚጠበቅበትን እንዲያበረክት እየሰራ ይገኛል፡፡
ሰላም በሌለበት ጤናማና የተረጋጋ ቢዝነስ መስራት ስለማይቻል በሰላም ላይ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ም/ቤቱ ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ ከ The Ethiopian Conflict Sensitivity Hub ጋርም በዚህ ላይ አብሮ ለመስራት ከስምምነት መደረሱን የሁለቱም ወገን ተወያዮች አስረድተዋል፡፡
በሌላ መልኩ በሰላም ግንባታና ለግሉ ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦትን ማመቻቸት በሚቻልበት ሁኔታም ላይ በአለም ባንክ ከ International Finance Corporation (IFC) ጋርም የም/ቤቱ ዋና ፀሐፊ ተወያይተዋል፡፡

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) hold discussion with development partners about making things easier for private businesses.
The Secretary General of ECCSA, Dr. Kenenisa Leme, talking with development partners The Ethiopian Conflict Sensitivity Hub (ECSH) and International Finance Corporation (IFC), said there should be a good business environment so that the private sector can properly contribute to the country’s economic growth and make the expected contribution.
The Ethiopian Conflict Sensitivity Hub (ECSH) is a non-profit that looks at the root causes of conflict and the absence of peace, focusing mainly on peace-building activities. The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations is also teaming up with the Ministry of Peace and other stakeholders by creating the Business for Peace Initiative and is working with them to help keep peace by involving private sectors in the peace building process.
On the other hand, ECCSA’s Secretary General also talked with the International Finance Corporation (IFC), the member of World Bank group on the facilitation of access to Finance for private sectors.

