Jul 31, 2026 .
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የግሉ ዘርፍና መላዉ የንግዱ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና በንቃት እንዲሳተፉ – አቶ ሰብስብ አባፊራ

ኢትዮጵያዉን በተባበረዉ ክንዳቸዉ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ለጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ምላሽ የሚሰጡበት ቀን እየደረሰ ነዉ።
ሁሌም እንደ አገር አዲስ ታሪክ ለመሥራት ለሚደረገዉ ጥሪ በግንባር ቀደምትነት ምላሽ የሚሰጠዉ የግሉ ዘርፍና መላዉ የንግዱ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና በንቃት እንዲሳተፉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በጋራ ተስፋን እንትከል!

