Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 31, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ የIFRS ስልጠና በዘርፉ እዉቅ ባለሙያዎች

የዓለም አቀፍ የሒሳብ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS – International Financial Reporting Standards) ለተቋማት፣ ለኢንቨስተሮች እና ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የሚከተሉት  ዋና ዋና ጥቅሞች አሉት።

1. ተወዳዳሪነት እና ንፅፅር (Comparability) IFRS የተለያዩ ኩባንያዎች ተመሳሳይ የሂሳብ አሰራር እና የሪፖርት አቀራረብ እንዲከተሉ ያደርጋል። ይህም ኢንቨስተሮች እና ባለድርሻ አካላት የተለያዩ ኩባንያዎችን የፋይናንስ አፈፃፀም በቀላሉ ጎን ለጎን አነፃፅረው እንዲገመግሙ ይረዳቸዋል።

2. ግልጽነት እና ተአማኒነት (Transparency & Reliability)
የፋይናንስ መግለጫዎች ግልጽ፣ ጥራት ያላቸው እና አለም አቀፍ መስፈርትን የጠበቁ እንዲሆኑ ያደርጋል። ይህም የመረጃ መደባበቅን ወይም የተሳሳተ ሪፖርት አቀራረብን በመቀነስ የተቋማቱን ተአማኒነት ይጨምራል።

3. የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ (Attracting Foreign Investment) አለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የፋይናንስ ሪፖርታቸውን በ IFRS የሚያዘጋጁ ሀገራት እና ኩባንያዎች ላይ በራስ መተማመን ኢንቨስት ያደርጋሉ። የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች አለም አቀፍ የሂሳብ ስታንዳርድ ሲከተሉ የውጭ ካፒታል በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ።

4. የካፒታል ወጪን መቀነስ (Lower Cost of Capital) ግልጽ እና ተአማኒ የፋይናንስ መረጃ የሚያቀርቡ ኩባንያዎች ከባንኮችና ከኢንቨስተሮች ብድር ወይም ካፒታል ሲጠይቁ የሚጠየቁት የካፒታል ወጪ (ወለድ ወይም አደጋ/risk margin) አነስተኛ ይሆናል።
5. የተሻለ የውሳኔ አሰጣጥ (Better Decision Making) ለተቋማት አመራሮች፣ ባለአክሲዮኖች እና አበዳሪዎች ትክክለኛ እና ወቅታዊ የፋይናንስ መረጃ በመስጠት የተሻለ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ውሳኔ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል።

በአጠቃላይ IFRS የፋይናንስ ስርዓቱን በመቅረፅ የንግድ እንቅስቃሴዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በስኬት እንዲካሄዱ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ሁሌም የግሉን ዘርፍ ሁለንትናዊ አቅም በመገንባት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ወቅቱን የዋጁ ስልጠናዎችን በመስጠት የሚታወቀዉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ የግሉ ዘርፍ የሒሳብ ሪፖርት ስርዓታቸዉን አለምአቀፋዊ በሆነ መልኩ እንዳያዘጋጁ የሚያስችላቸዉን የIFRS ስልጠና በዘርፉ እዉቅ ባለሙያዎች ለመስጠት አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ምዝገባ እያካሄደ ነዉ።

ስለሆነም በመስኩ ለመሰልጠን ፍላጎት ያላችሁ ባለሙያዎችና ሰራተኞቻችሁን ማሰልጠን የምትፈልጉ ተቋማት እስከ ነሐሴ 2/2018 ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia