Aug 04, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በቢዝነስ ትንተና መተግበሪያ (Power Business Intelegence” ዙሪያ ሥልጠና እየሠጠ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በቢዝነስ ትንተና መተግበሪያ (Power Business Intelegence” ዙሪያ ሥልጠና እየሠጠ ነው።
ሥልጠናው መረጃን በአግባቡ ለመተንተንና የቢዝነስ ዳሰሳ (Business Analytics) በማድረግ ትክክለኛና ሊተገበር ወደ ሚችል መረጃ መቀየር በሚያስችል አሠራር ዙሪያ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙትብየምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ምክር ቤቱ በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ በኩል ለግሉ ዘርፍ ሥልጠና እየሠጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለንበት የመረጃ ዘመን የተገኘን ጥሬ መረጃ በመተንተን ለውሳኔ እንዲያመች ማድረግ እና መረጃን በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ተገቢ መሆኑን በመግለጽ ስልጠናው ውጤት ማምጣት የሚያስችል እድል ሥለመሆኑ ጠቁመዋል።
ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የሚወስዱት ሥልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ነው።
Power BI ጥሬ መረጃዎችን ወደ ግልጽ ሪፖርቶች በመቀየር ለድርጅቶችና ለግለሰቦች ስራቸውን በቀላሉ ለመረዳትና ለመገምገም የሚያስችል የማክሮሶፍት (Microsoft) መተግበሪያ መሆኑ ይታወቃል።

