Aug 05, 2026 .
2018 ዓ.ም. “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ጥሪን በከፍተኛ ቁርጠኝነትና በንቃት በመቀበል፣ ያደረጋችሁት አስደናቂ እና ተምሳሌታዊ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ክብር የሚገባው ነው።

በመላው ኢትዮጵያ በፌዴራል፣ በክልልና በየደረጃው ለምትገኙ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ ሠራተኞች እና በተለይም መላው የንግዱ ማህበረሰብ፤
በ2018 ዓ.ም. “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ሀገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ጥሪን በከፍተኛ ቁርጠኝነትና በንቃት በመቀበል፣ በግንባር ቀደምነት ችግኝ በመትከል ለመርሃ ግብሩ ስኬት ያደረጋችሁት አስደናቂ እና ተምሳሌታዊ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ክብር የሚገባው ነው።

የእናንተ ተሳትፎ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለዘላቂ ልማት እና ለትውልድ የሚተርፍ አረንጓዴ ቅርስ ግንባታ የተደረገ ውድ አስተዋፅኦ መሆኑን በኩራት መግለፅ እወደዋለሁ ።
ለዚህም በኢትዮጽያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን ከታላቅ አክብሮት ጋር ማቅረብ እወዳለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

