Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 31, 2026 .

የኢትዮጵያ ቢዝነሶች በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ቢዝነሶች በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቋል።

በሥልጠናው ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች፣ አስመጪዎችና ላኪዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ቢዝነሶች በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) አተገባበርና ፕሮቶኮሎችን በአግባቡ መረዳትና አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ሥልጠናውም በAfCFTA ማዕቀፍ የወጭ ንግድን በአግባቡ ስለማከናወን፣ የስምምነቱን አሠራሮች ስለመረዳትና ከአፍሪካ ገበያ የሚገኙ የንግድ ዕድሎችን ስለመጠቀም ያተኮረ ነበር።

የስምምነቱ 21ኛ ፈራሚ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶቿን ወደ አፍሪካ ሀገራት በመላክ የንግድ እንቅስቃሴዋን እያሳደገች ትገኛለች።

ይህንን ዕድል በሰፊው ለመጠቀም ግን የግሉ ዘርፍ የስምምነቱን የንግድ ሥርዓትና ፕሮቶኮሎች በጥልቀት መረዳት ይጠበቅበታል።

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ከAfCFTA ባሻገር ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን በሂደት ላይ መሆኗን በመገንዘብ፣ በአፍሪካና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን ከወዲሁ መዘጋጀትና አቅሙን ማሳደግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ነጋዴዎችና አምራቾች በአፍሪካ ገበያ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የAfCFTA አሠራርን በአግባቡ መረዳታቸው ወሳኝ መሆኑን፣ ሥልጠናውም ይህንን አቅም ለመፍጠር ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

የሥልጠናው ተሳታፊዎችም በAfCFTA ማዕቀፍ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዙ ዕውቀትና ግንዛቤዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia