Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 01, 2026 .

ከሃንጋሪና ከዩክሬን የዲፕሎማሲና የንግድ ተወካዮች ጋር የተካሄዱ ውይይቶች ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ ትብብር ለማስፋት ያለውን ትልቅ ዕድል ያመላክታሉ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ ከዓለም አቀፍ የንግድና የኢንቨስትመንት ማኅበረሰብ ጋር ለማስተሳሰር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል።

ዛሬም ከሃንጋሪና ከዩክሬን የዲፕሎማሲና የንግድ ተወካዮች ጋር የተካሄዱት ውይይቶች በኢትዮጵያና በእነዚህ አገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ ትብብር ለማስፋት ያለውን ትልቅ ዕድል ያመላክታሉ።

በኢትዮጵያ በግብርናና በምርት ማቀነባበር፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በፋርማሲዩቲካል፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች በርካታ ዘርፎች ለተሰማሩ የውጭ ባለሀብቶችና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ሰፊ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎች አሉ።

ይህንን እምቅ ዕድል ወደ ተጨባጭ የንግድ አጋርነት መቀየር የግሉ ዘርፍን ተወዳዳሪነትና የኢኮኖሚውን ዘላቂ ዕድገት ለማጠናከር ወሳኝ ነው።

ስለሆነም ምክር ቤታችን በኢትዮጵያና በሌሎች አገራት የግሉ ዘርፍ መካከል የቢዝነስ ትስስርን ለማጠናከር፣ የኢንቨስትመንት አጋርነቶችን ለማስፋፋት፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ለማበረታታት እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን ቢዝነሶች አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን ለመፍጠር ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አጠናክሮ ይቀጥላል።

በዚህ መሠረት፣ 16ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያና የውጭ አገራት ኩባንያዎች፣ ባለሀብቶችና የንግድ ተቋማት በቀጥታ ተገናኝተው የጋራ የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን የሚያዩበት ጠቃሚ መድረክ ነው።

በዚህ አጋጣሚ፣ የሃንጋሪ፣ የዩክሬንና የሌሎች አገራት ኩባንያዎች በዚህ መድረክ በመሳተፍ ከኢትዮጵያውያን የንግድ ተቋማት ጋር ዘላቂና የጋራ ጥቅም ያለው አጋርነት እንዲፈጥሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት
❇️❇️❇️❇️
The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations is strengthening its efforts to connect Ethiopia’s private sector with the global business community.

Today’s engagements with diplomatic and business representatives from Hungary and Ukraine reaffirm the significant potential for expanding trade, investment, technology transfer, and business partnerships between Ethiopia and these countries.

Ethiopia offers substantial investment opportunities across agriculture and agro-processing, leather and leather products, textiles and garments, pharmaceuticals, tourism, technology, and other key sectors.

Turning these opportunities into concrete partnerships will strengthen the competitiveness of our private sector and contribute to sustainable economic growth.

Our Chamber remains committed to expanding international business linkages, attracting investment, facilitating technology and knowledge transfer, and opening new markets for Ethiopian businesses.

The 16th Ethio-Chamber International Trade Fair will provide an important platform for businesses and investors to connect and explore mutually beneficial opportunities.

I therefore invite companies from Hungary, Ukraine, and other countries to participate and build lasting partnerships with Ethiopian businesses.

Sebsib Abafira Abajobir

President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia