Sep 07, 2026 .
ለመላው የግሉ ዘርፍ እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

ለመላው የግሉ ዘርፍ እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ!
ኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፋን ወደ ዘላቂ እድገት ለማሸጋገር የሚያስችሉ መሰረታዊ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እየከወነች ትገኛለች። በዚህ ሂደትም የግሉ ዘርፍ የሚጠበቅበትን ለመወጣት፤ በተለይም በምርት ማሳደግ፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በወጪ ንግድ ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፋት እንዲሁም በፈጠራ ላይ የሚያተኩር ሰፋፊ ተግባራትን ከምን ግዜው በተሻለ እየሰራ ነው።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም የግሉ ዘርፍን ድምፅ ተደማጭነት በማሳደግ ፣ የመንግሥትና የንግዱን ማኅበረሰብ ውይይት በማጎልበት እና ለንግድ የተሻለ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።
እየተካሄደ ያለው ሪፎርም በኢትዮጵያ የተሻለ የንግድ ምህዳር፣ የበለጠ ተወዳዳሪ የግሉ ዘርፍ እና ለዜጎች የተሻለ የኑሮ ዕድል የሚፈጥር እንዲሆን ሁላችንም የየበኩላችንን ሚና መወጣት ይኖርብናል። መጪው ዓመትም የተሻለ የንግድ ከባቢ፣ የተስፋፋ ኢንቨስትመንት፣ የበለጠ ምርታማነት፣ የተሻለ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እና በርካታ የስራ ዕድሎች የሚፈጠሩበት ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ።
አመሰግናለሁ!
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

