በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስር በሸቀጦች ለመነገድ የሚረዳ የደረጃ በደረጃ መመሪያ(Step-by-Step Guide) እየተካሄደ ነው፡፡


በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስር በሸቀጦች ለመነገድ የሚረዳ የደረጃ በደረጃ መመሪያ(Step-by-Step Guide) እና “የዲጂታል የንግድ መረጃ ፖርታል” ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ በስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡
መመሪያው ነጋዴዎች በAfCFTA ስር ሸቀጦችን ለመነገድ ስለሚያስፈልጉ ሂደቶችና መስፈርቶች ተግባራዊ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን፣ የአምራች ሀገር ሕግ (Rules of Origin) ፣ የጉምሩክ ሥርዓት፣ የሰነድ አያያዝ፣ የወጪ ንግድ ፈቃድና ማረጋገጫ እና ሌሎችንም መረጃዎች ያካትታል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ (Step-by-Step Guide እና የመረጃ ፖርታል በሴቶችና በወጣቶች ለሚመሩ ቢዝነሶች ጠቃሚ መረጃዎችን እንደሚሰጥ በመጠቆም መመሪያው እነዚህ የንግድ ተቋማት በስምምነቱ ስር ከሚካሄደው ንግድ ጋር የተያያዙ እድሎችን፣ አሰራሮችን እና መስፈርቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው፤ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማስፋት፣ እና አካታች የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት፣ የአነስተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

A workshop focusing on Ethiopia’s Step-by-Step Guide for Trading in Goods under the African Continental Free Trade Area (AfCFTA) and the Digital Trade Information Portal is being held in Addis Ababa.
The workshop is aimed at helping businesses better understand the procedures and requirements for trading goods under the AfCFTA.
The guide provides practical information on areas including rules of origin, customs procedures, documentation, export licences and certification, among other requirements.
Opening the workshop, Minister of Trade and Regional Integration Dr Kassahun Gofe said the guide and digital trade information portal would provide useful information for businesses led by women and young entrepreneurs.
He said the resources would help businesses gain a better understanding of the opportunities, procedures and requirements associated with trading under the AfCFTA.

Dr. Kenenisa Lemi, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), said providing businesses with adequate information would be important for expanding Ethiopia’s exports and promoting more inclusive economic growth.
He said chambers of commerce have an important role to play in helping businesses, particularly small and medium-sized enterprises, understand and make use of opportunities in the African market.
Dr. Kenenisa reaffirmed ECCSA’s readiness to support Ethiopian businesses by providing the necessary information and assistance to enable them to participate more effectively in AfCFTA trade.

