Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 28, 2026 .

የኣትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮመርስ ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኣትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከሳይፕ ኢትዮጵያ (CIPE-Ethiopia) ጋር በመተባበር በጅማ ከተማ ከግሉ ዘርፍ ለተዉጣጡ በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮመርስ ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በስልጠናዉ መጨረሻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያለንበት ዘመን የዲጂታል ዘመን እንደመሆኑ መጠን የንግዱ ማህበረሰብ በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ኢ-ኮመርስ በቂ ግንዛቤ እና ዕዉቀት ኖሮት ለሚጠብቀዉዐብርቱ ፉክክር እራሱን ማዘጋጀት አለበት ብለዋል።

የስልጠናዉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በአሁኑ ወቅት በርካቶች ከፍለዉ የሚሰለጥኑትን ወቅቱን የዋጀ ስልጠና ም/ቤቱ በነፃ ስላመቻቸላቸዉ አመስግነዉ ለወደፊቱም የንግዱን ማህበረሰብ የተወዳዳሪነት አቅም የሚያሳድጉ ስልጠናዎች መኖር አለባቸዉ ብለዋል።

ምክር ቤቱ የሚሰጣቸዉ ስልጠናዎች ሁሉንም ያማከለ ሲሆን በተለይም የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኛ ቢዝነስ አንቀሳቃሾችን አቅም ለመገንባት ትኩረት እንደሚሰጥም ዶ/ር ቀነኒሳ ገልፀዋል።

በተለይም ደግሞ ይህ ስልጠና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገና አካታች መሆኑ ሊበረታታ የሚገባ መሆኑንም ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia