የአጀንዳ ምክረ-ሀሳቦች ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለየክልል ርዕሳነ- መስተዳድሮች የማስረከብ መርሐ -ግብር ትናንት ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፣ የግሉ ዘርፍ እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከተሳተፋበት ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች የተገኙ የአጀንዳ ምክረ-ሀሳቦች ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለየክልል ርዕሳነ- መስተዳድሮች የማስረከብ መርሐ -ግብር ትናንት ተከናውኗል።
ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ሰነድ 81 ጉዳዮች ላይ የቀረቡ 400 ዝርዝር ምክረ-ሀሳቦችን የያዘ ነው።
በአጀንዳና በምክረ-ሀሳብ ርክክብ መድረኩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል ።
❇️❇️❇️❇️❇️
ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክልል መንግሥታት በይፋ ርክክብ የተደረገበትን መርሃ ግብር ዛሬ ተከታትያለሁ።
ይህ የሰነድ ርክክብ ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚያስመዘግብ ሲሆን የኢትዮጵያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎች አካታች በሆነ ውይይት፣ በሰላማዊ ምክክር እና በራሳችን ሀገር በቀል የመፍትሔ አምጭ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።
❇️❇️❇️❇️❇️
Sagantaa qabxiiwwan ajandaafi yaadota gorsaa Marii Biyyaalessaa Itoophiyaarra argaman Mana Maree Bakka Bu’oota Uummataa, Mootummaa Federaalaafi Mootummoota naannoleef ifatti dabarfamanii itti kennaman irratti argamee hordofeera.
Walharkaa fuudhinsi sanadaa kun adeemsa Marii Biyyaalessaa keessatti boqonnaa faayidaa qabeessa kan agarsiisu yoo ta’u, qormaatilee Itoophiyaa yeroo dheeraaf turan marii haammataa ta’een, karaa naga-qabeessaan, akkasumas furmaata biyyarraa maddeen hiikuudhaaf murannoo qabnu irra-deebiidhaan kan mirkaneessedha.
❇️❇️❇️❇️❇️❇️
Today, I attended and oversaw the formal handover of the consolidated agenda items and recommendations emerging from Ethiopia’s National Dialogue to the House of Peoples’ Representatives, the Federal Government, and Regional Governments.
This handover marks an important milestone in the National Dialogue process and reaffirms the commitment to addressing Ethiopia’s longstanding challenges through inclusive dialogue, peaceful deliberation, and nationally owned solutions.
ክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

