Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 07, 2026 .

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ክቡር ዐብይ አህመድ አሊ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመሰየማቸው የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ክቡር ዐብይ አህመድ አሊ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመሰየማቸው የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በመልዕክታቸው ፤ በእርስዋ የአመራር ዘመን ኢትዮጵያ የገጠሙዎትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በመጋፈጥና በአሸናፊነት በመውጣት የአገራችን ኢኮኖሚ እንዲሻሻል፣ የኢኮኖሚ መሠረቶች እንዲጠናከሩና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የበለጠ እንዲጎለብት ለተወሰዱት ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችና ለተገኙት ውጤቶች ያለንን አድናቆትና ምስጋና እናቀርባለን ተብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ለውጥና ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማደግ የተወሰዱ እርምጃዎች፣ ገበያ-ተኮርና ውድድርን ወደሚያበረታታ ስርዓት ለማሸጋገር የተሰሩ ስራዎች፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እንዲሁም የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የውስጥ ገቢን ለማሳደግ የተደረጉ ጥረቶች፣ የመንግስት ድርጅቶችን አፈጻጸምና አስተዳደር ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች እንዲሁም ለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የተከፈቱ የኢንቨስትመንትና ንግድ ዕድሎች አገራዊ ጠቀሜታቸው የጎላ መሰረታዊ ለውጦች ናቸው።

ከዚህም ባሻገር ፤ የቴሌኮምና የሎጂስቲክስ ዘርፎችን ለውድድር መክፈት፣ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ተሳትፎ ማዘጋጀት፣ የፋይናንስ ስርዓቱን ማዘመን እና የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛ አጋር እንዲሆን የተወሰዱ አቅጣጫዎችም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የበለጠ ክፍትና ተወዳዳሪ ለማድረግ አግዘዋል።

እንዲሁም ፤ በቅርቡ ተጠናክረው የቀጠሉት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን የማሻሻል፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያ መዛባትን የመቀነስ፣ ኤክስፖርትን የማሳደግና የዋጋ ንረትን የማረጋጋት ሁሉ አቀፍ ተግባራት ያስገኙት ውጤት በዓለም ባንክ( WB) እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(IMF) ምስክርነት ያገኙ ውጤቶች ናቸው።

እነዚህ ለውጦች በተለያዩ የኢኮኖሚ፣ የፀጥታ፣ የጤና፣ የአየር ንብረትና የዓለም ገበያ ተጽዕኖዎች ውስጥ መከናወናቸው የስራውን አስቸጋሪነት ከማሳየቱ አንፃር የተገኘው ውጤት ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው።

በቀጣዩ የአመራር ዘመንዎም የተጀመሩትን ማሻሻያዎች በማጠናከርና የንግድ ስራ ምቹነትን ማሻሻል፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ፣ የምርታማነትና የኤክስፖርት አቅምን ማስፋት፣ የሎጂስቲክስና የፋይናንስ ወጪዎችን መቀነስ፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና የግሉ ዘርፍ በፖሊሲ ውሳኔዎች ውስጥ የሚኖረውን ተሳትፎ ማጠናከር ቀዳሚ ትኩረቶች እንደሚሆኑ ሙሉ እምነት አለን።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በዚህ አጋጣሚ መንግስትና የግሉ ዘርፍ በጋራ በመሥራት የአገራችንን የኢኮኖሚ አቅም ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል ተቋማዊ አጋርነት ለማጠናከር ያለውን ዝግጁነት ያረጋግጣል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ባለፈው የአመራር ዘመን ለአገራችን ኢኮኖሚ ማሻሻያና ለውጥ የተደረገውን ጥረት በማመስገን፣ በቀጣይ ዘመንም ኢትዮጵያ የተረጋጋ፣ ተወዳዳሪ፣ ምርታማና የግሉ ዘርፍ በሙሉ አቅሙ የሚሳተፍበት ኢኮኖሚ እንድትገነባ አብረን ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት እንገልጻለን።

ለክቡርነትዎ በተሰጠው ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ጥበብ፣ ጥንካሬና ስኬት እንዲቸርዎ እየተመኘን፣ የአገራችን ሰላም፣ አንድነትና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ የሚጠበቅብንን ሁሉ እንደምንወጣ በድጋሜ እናረጋግጣለን ሲሉ አጠቃለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia