በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶክተር)

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ሥራ መጀመሩን ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው።
በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም ያለው ይህ የማጣሪያ ፋብሪካ፤ በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት ለመጨመር፣ የኢትዮጵያን የማዕድን ዘርፍ ለማጠናከር እና ሀገራችንን በውድ ማዕድናት ማጣሪያ ረገድ ቀጣናዊ ማዕከል ለማድረግ ለተጀመረው ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
ይህ ውጥን፤ ሀብቶቻችንን ከኢንዱስትሪ አቅም ጋር በማስተሳሰር ወጭ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ የሰለጠነ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ እንዲሁም ይበልጥ ግልጽ እና ተወዳዳሪ የሆነ የወርቅ እሴት ሰንሰለት ለመገንባት የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር ድረስ በሀገራችን ውስጥ የላቀ እሴት እየፈጠርን እንገኛለን።

I am proud to announce the launch of the National Precious Metals Refinery at Bole Lemi Special Economic Zone, established through a partnership between Ethiopian Investment Holdings (EIH) and Sam Precious Metals.
With a capacity to process over 600 tonnes of precious metals annually, the refinery marks a major milestone in advancing domestic value addition, strengthening Ethiopia’s mining sector, and positioning our country as a regional hub for precious-metals refining.

This initiative reflects the Medemer government’s commitment to linking our productive resources with industrial capacity—boosting export earnings, creating skilled jobs, supporting the jewellery industry, and building a more transparent and competitive gold value chain.
From resource extraction to industrial transformation, we are creating greater value at home.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶክተር)

