በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሶማሌላንድ የንግድ ምክር ቤት መካከል የመግባብያ ስምምነት ተፈረመ።

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የሶማሌላንድ የኢንሹራንስ ጉባኤና ኤክስፖ 2026 ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሶማሌላንድ የንግድ ምክር ቤት መካከል ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ዙሪያ በጋራ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የመግባብያ ስምምነት ተፈረመ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በፊርማ ስነ- ስርዐቱ ላይ እንደተናገሩት ስምምነቱ ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የንግድ ግንኙነቶችን እንዲያሳድጉ፣ አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን እንዲያገኙ እና የጋራ ኢንቨስትመንት አቅሞችን እንዲያስፋፉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያግዝ ነው።
ፕሬዚደንቱ አክለውም ፤ በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ምክር ቤቶች የንግድ መረጃ ልውውጥን ማሳደግ፣ የንግድ ልዑካን ጉብኝቶችንና የንግድ ቢዝነስ ፎረሞችን ማመቻቸት፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለባለሀብቶች ማስተዋወቅ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በጋራ ፕሮጀክቶችና የንግድ አጋርነቶች ላይ እንዲሳተፉ የሚያግዙ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ ይፈጥራል።
በተጨማሪም፣ ስምምነቱ በንግድ ዘርፎች የልምድና ዕውቀት ልውውጥን ለማበረታታት፣ በንግድ ሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመለየትና መፍትሔዎችን ለማፈላለግ ያስችላል።
የተፈራረምነው የመግቢያ ስምምነት ከዚህም ባሻገር የንግድ ማኅበረሰቦች መካከል ዘላቂ የንግድ አጋርነት መፍጠር፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፣ የገበያ ተደራሽነትን ማስፋፋትና አዳዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ዕድሎችን ማሳደግ ያስችላል።
ይህ የመግባቢያ ስምምነት በንግድ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ከመደበኛ ግንኙነት ወደ ተግባራዊ የንግድ ውጤት ለማሸጋገር፣ የግሉ ዘርፍን የኢኮኖሚ ልማት ሞተርነት ለማጠናከርና በክልሉ የጋራ ብልጽግናን ለማሳደግ ጠቃሚ እርምጃ ነው።
በዚህ አጋጣሚም፤ ለሶማሌላንድ የንግድ ምክር ቤት እና አመራሮች በምክር ቤታችን ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።


A Memorandum of Understanding (MoU) was signed between the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) and the Somaliland Chamber of Commerce, Industry and Agriculture on the sidelines of the second day of the Somaliland Insurance Summit and Expo 2026.The agreement aims to promote trade and investment and strengthen cooperation between the two institutions.
Speaking at the signing ceremony, H.E. Sebsib Abafira Abajobir, President of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, said the agreement would strengthen institutional cooperation and create favourable conditions for private sector actors to expand business relationships, access new markets and explore joint investment opportunities.
The President further explained that, under the agreement, the two chambers would establish a framework for cooperation encompassing the exchange of trade information, the facilitation of business delegation visits and business forums, the promotion of investment opportunities to investors, and joint initiatives to encourage private sector representatives to participate in collaborative projects and business partnerships.
He added that the agreement would also promote the exchange of knowledge and experience in the trade sector, enabling both institutions to jointly identify challenges facing businesses and explore practical solutions.
Beyond these areas, the MoU is expected to foster sustainable business partnerships between the two business communities, increase private sector participation, expand market access and create new opportunities for economic cooperation.
The agreement represents an important step towards translating institutional cooperation into tangible business outcomes, strengthening the private sector’s role as an engine of economic development and advancing shared prosperity across the region.
On the occasion, the President expressed his appreciation, on behalf of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, to the Somaliland Chamber of Commerce and its leadership for their cooperation and commitment to strengthening the partnership.

