Oct 19, 2026 .
ከትግራይ ክልል ባላደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር ዉይይት አካሂደናል- የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ

በፌደራል መንግስት ከተሰየሙት የትግራይ ክልል ባላደራ አስተዳደር ፤ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ ከተከበሩ አቶ አሰፋ አብራሃ እና ሌሎች የክልሉ ባላደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር በአገር አቀፍ የአገር ሽማግሌዎች ቢሮ የባላደራ አስተዳደሩን እና የክልሉን ሕብረተሰብ በምንደግፍበት ሁኔታ ላይ ጥሩ ዉይይት አካሂደናል።
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

