Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 27, 2026 .

የሀዋሳ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ‎በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤንባሲ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ውይይት ማካሄዱን አስታወቀ።

የሀዋሳ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ‎በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤንባሲ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ውይይት ማካሄዱን አስታወቀ።
‎
በሀዋሳ ኃይሌ ሪዞርት በተካሄደዉ ዉይይት ላይ ‎የሀዋሳ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ በረከት ጎኔ ክልሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በሆነው የሲዳማ ቡና፣ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ማዕከል ለባለሀብቶች ምቹ የሆኑ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንደሚፈጥሩ አስረድተዎል።

አያይዘውም የከተማው የንግድ ማህበረሰብ ተወዳዳሪ እንዲሆን፣ ከሀገር እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ ለንግድ ትስስር (B2B) እንዲፈጠር እና የክልሉ ምርቶች ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ በሰፊው እና በትኩረት እንደሚሰሩ አጽንኦት ተሰጥተዋል።


‎
‎ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤንባሲ የ Public Diplomacy Counselor አድሪያን ኑትዝማን በበኩላቸው በሀዋሳ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ኤንባሲው ከንግድ ምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የግሉን ዘርፍ በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ማብቃት፣ የገበያ እና የንግድ ለንግድ ግንኙነትን (B2B) ማጠናከር እንዲሁም የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልውውጥ ማድረግ ላይ ለመስራት ተወያይተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia