ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ፣ በአሜሪካ እያደረጉ ያሉት የአመራር ብቃት ማሳደጊያ ጉብኝት የምክር ቤቱን ተቋማዊ አቅምም ሆነ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማጠናከር በሚያደርጉት ተሳትፎ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገለጹ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ፣ በአሜሪካ እያደረጉ ያሉት የአመራር ብቃት ማሳደጊያ ጉብኝት የምክር ቤቱን ተቋማዊ አቅምም ሆነ አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማጠናከር በሚያደርጉት ተሳትፎ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገለጹ።
ዶ/ር ቀነኒሳ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በፖርትላንድ ሜይን እና በዳላስ ቴክሳስ እንዲሁም በማያሚ ፍሎሪዳ የአመራር ብቃት ማሳደጊያ እንዲሁም የተቋማት ጉብኝት በማድረግ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ።
የጉብኝቱ መርሐ ግብር ከአሜሪካ ተቋማት ተሞክሮ ለመቅሰም፣ የትብብር መስኮችን ለመለየት እና ለወደፊት የጋራ ሥራዎች መሠረት የሚሆኑ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ጠቃሚ ዕድሎችን እንደፈጠረላቸውም ገልጸዋል።
ዋና ፀሐፊው ከተለያዩ ተቋማት የተገኘው ልምድና የተቋማዊ አሠራር ተሞክሮ፣ የንግዱን ማኅበረሰብ የመወከልና ጥቅሙን የማስጠበቅ ተልዕኮ ላለው ምክር ቤቱ ጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል።
በመጨረሻም፤ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በጉብኝቱ የተገኘውን ዕውቀትና ልምድ ወደ ተግባራዊ ውጤት በመቀየር ለምክር ቤቱ ተቋማዊ ዓላማዎችና ለኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

Dr. Kenenisa Lemi, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, has said his leadership development visit to the United States will contribute to strengthening the Chamber’s institutional capacity and supporting Ethiopia’s broader economic development.
Dr. Kenenisa is undertaking leadership development training and institutional visits in Washington, D.C., Portland, Maine, Dallas, Texas, and Miami, Florida, as part of the programme, which provides opportunities for professional learning and experience sharing.
He said the visit had created valuable opportunities to learn from the experiences of American institutions, identify potential areas of cooperation and establish relationships that could serve as a foundation for future partnerships.
The Secretary General noted that the institutional practices and experiences gained during the visit were particularly relevant to ECCSA’s mandate of representing the business community and safeguarding its interests.
He also highlighted the importance of applying the knowledge and experience gained to strengthen the Chamber’s institutional objectives and contribute to the development of Ethiopia’s economy.
Dr. Kenenisa expressed his gratitude to the US Department of State for facilitating the programme, reaffirming his commitment to translating the experience into practical results for ECCSA and the country’s wider economic development.
