በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በድሬዳዋ ከተማ እየተሠጠ ነው።


በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በድሬዳዋ ከተማ እየተሠጠ ነው።
………………………
ስልጠናው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት (ECCSA) ከGIZ AU እና ከድሬዳዋ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ ያተኮረ ነው።
የስለጠናዉ ተሳታፊዎችም በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ ላኪዎች፣ አስመጪዎች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ናቸው።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ ስልጠናው የከተማችን ነጋዴዎች በአፍሪካ ገበያ ዉስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ስልጠናዉን በዚህ መልኩ ለከተማችን ነጋዴዎች አዘጋጅቶ መስጠቱ የሚያስመሰግነዉ ነዉዐብለዋል።
በGIZ/AU የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማካሪ አቶ ዉብሸት ካሳ በበኩላቸው፣ ስልጠናው የክልሉ ነጋዴዎች ስለAfCFTA በቂ ዕውቀት እንዲያገኙና በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናውን የሚሰጡት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጡ በዘርፉ ሰፊ ሙያዊ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ናቸው።
የነጋዴው ማኅበረሰብ የAfCFTA ስምምነት ፕሮቶኮሎች፣ የንግድ ሂደቶችና የስምምነቶቹን የመተግበሪያ ሂደቶች በአግባቡ እንዲረዳ ማድረግ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ ነዉ።

