Aug 19, 2026 .
ቀልጣፋ እና ምቹ የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥ በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ትልቅ ሚና አለው፦ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ

ቀልጣፋ እና ምቹ የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥ በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ትልቅ ሚና አለው፦ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በደንበኛ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ (Customer Service) ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቋል።
የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት፣ ውጤታማና ምቹ የደንበኛ አያያዝ ለንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ለተቋማዊ ዘላቂ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ አለው።

በዘመናዊ የንግድ አሠራር ውስጥ “ደንበኛ ንጉሥ ነው” የሚለውን መርህ በተግባር መተርጎም የተቋማትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ተመራጭ ለመሆን የደንበኛ አያያዝን ማሻሻል፣ ጥራትንና ደህንነትን ማረጋገጥ እንዲሁም አቀባበልና አገልግሎትን (Hospitality) የተሻለ ማድረግ እንደሚገባ ዶ/ር ቀነኒሳ ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ የግሉን ዘርፍ አቅም ለማሳደግ በቢዝነስ አመራር አካዳሚው በኩል በተለያዩ የንግድና አመራር ዘርፎች ሥልጠናዎችን እየሰጠ ሲሆን ሁለተኛው ዙር የደንበኛ አገልግሎት (Customer Service) ሥልጠና ከነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

