ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከቻይናው CCCC ኩባንያ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ልማት (Cold Chain Development) ኩባንያ ኃላፊ ሹ ሀይፌይ ጋር ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት (ECCSA) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከቻይናው CCCC ኩባንያ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ልማት (Cold Chain Development) ኩባንያ ኃላፊ ሹ ሀይፌይ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የአቮካዶ ምርትና ማቀነባበር ዘርፍ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ተነጋግረዋል፤፡፡
የአቮካዶ ምርት፣ ማቀነባበር፣ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት መሠረተ ልማትና ከዘርፉ ጋር ተያያዥ የእሴት ሰንሰለቶችን በማልማት ረገድ ያሉ የኢንቨስትመንትና ትብብር እድሎች በስፋት ተነስተዋል።
ኃላፊው ሹ ሀይፌይ CCCC የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ልማት (Cold Chain Development) ኩባንያ ከኢትዮጵያ አቮካዶ አምራቾች እና በአቮካዶ ምርት ላይ ከሚሰሩ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።
ከምርት አያያዝ፣ ማከማቻና ሎጂስቲክስ ማሻሻል እዲሁም የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ በትብብር ለመስራት እንደሚፈልጉም ተናግረዋል፡፡
ዋና ጸሐፊው ዶ/ር ቀነኒሳ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ብሔራዊ የአቮካዶ ልማት መርሃ ግብር ለሊቀመንበሩ አብራርተውላቸዋል፡፡
በአቮካዶ ምርትና ማቀነባበር ዘርፍ ያሉትን የኢንቨስትመንት እድሎች ያብራሩት ዋና ጸሐፊው ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ አካባቢ እንዳላትና የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎች ስለመኖራቸው ገልጸውላቸዋል፡፡
ምክር ቤቱ የውጭ ኩባንያዎችን ከኢትዮጵያውያን የኢንቨስትመንት ማኅበረሰብ ጋር በማገናኘት፣ ያሉትን እድሎች በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡
በውይይቱ የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ እና ሌሎች የምክር ቤቱ ባለሙያዎችም ተገኝተዋል።

Dr. Kenenisa Lemie, Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), held a meeting with Mr. Shou Haifei, Chairman of China Communications Construction Company Limited (CCCC) Cold Chain Development Co., Ltd., to discuss investment opportunities in Ethiopia’s avocado sector.
The two sides discussed the potential for investment and development in avocado production, processing, cold-chain infrastructure, and related value chains, as well as ways to further improve the business and investment environment.
Mr. Shou Haifei expressed his company’s strong interest in working with Ethiopian avocado producers and other stakeholders engaged in avocado production. He also highlighted opportunities for cooperation in cold-chain development and management, which are essential for post-harvest handling, storage and logistics.
Dr. Kenenisa briefed the chairman on Ethiopia’s national avocado development program and highlighted the growing opportunities available for investment in avocado production and processing. He also highlighted the country’s conducive investment environment and the significant potential for Chinese companies to invest in Ethiopia.
He also underscored the commitment of ECCSA to facilitating trade and investment by connecting investors with Ethiopian businesses, promoting available investment opportunities, and advocating for continuous improvement of the country’s business environment.
The Deputy Secretary General, Mrs. Helen Reta, along with other ECCSA staff members, also attended the meeting.

