Jul 24, 2026 .
በዲጂታል ግብይት እና የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ላይ ስልጠና ተካሄደ::

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ (CIPE) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በዲጂታል ግብይት እና የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ላይ ከጥቃቅን፤ አነስተኛ፤ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ለተውጣጡ 20 የሚሆኑ የንግድ ማህበረሰብ ከሀምሌ 16-17 ቀን ፣2018 አ.ም ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡


ቴክኖሎጂ በንግድ ውስጥ የሚኖረውን ሚና መረዳት እና መጠቀም; ስለ ኤሌክትሮኒክ ንግድ (e-commerce) መረዳት እና በተግባር ማዋል; በኤሌክትሮኒክ ግብይት (E-Marketing) ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ዋና ዋና መሳሪያዎችን፣ ዘዴዎችን እና ተግባራት መለየት; የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕቀፎችን እና ስልቶችን በተግባራዊ ሁኔታዎች ላይ መተግበር; በዋና ዋና የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሙያዊ የንግድ ገጾችን መፍጠር እና ማስተዳደር; ለታለመላቸው ታዳሚዎች የተዘጋጁ የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን መንደፍ እና ማስኬድ የዚህ ስልጠና ዋና ዋና ዓላማዎች መሆናቸውን በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ ጠቁመዋል።

