Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 23, 2026 .

የ2018 አመታዊ  የሥራ አፈጻጸም እንዲሁም የ2019 የትኩረት አቅጣጫና ተቋማዊ ዝርዝር እቅድ  ላይ ከምክር ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር ግምገማዊ ውይይት (Review discussion) አካሂደናል:- ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የ2018 አመታዊ  የሥራ አፈጻጸም እንዲሁም የ2019 የትኩረት አቅጣጫና ተቋማዊ ዝርዝር እቅድ  ላይ ከምክር ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር ግምገማዊ ውይይት (Review discussion) አካሂደናል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም፤  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለአገራዊ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያችን ሁለንተናዊ ስኬት አስተዋጽዖ ባደረጉ ተግባራት ፤   ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና ለአገር ውስጥ ምርቶች የገበያ መዳረሻ በመፈለግና የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ  የተከናወኑ ስራዎች በበጀት ዓመቱ ውጤታማ አፈፅፀም ማስመዝገብ የተቻለባቸው መሆኑ ተለይቷል።

በሌላም በኩል ፤ ከአባል ምክር ቤቶች፣ ከሚመለከታቸው  የሚንስቴር መስርያ ቤቶች እና ከባለድርሻ አካላት እንዲሁም  በተዋረድ ከክልል ንግድ ጽ/ቤቶች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር  የተከናወኑ ተግባራት ውጤት አምጥተዋል።

ከዚህም ባሻገር፤  በየደረጃው የሚገኙ አባል የንግድ ምክር ቤቶቻችንን በማደራጀት፣  መልሶ በማጠናከርና የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በማከናወን ረገድ ውጤት ያስገኙ ስራዎች ተከናውነዋል ::

በሌላም በኩል ፤ የ2019 የበጀት ዓመት ዕቅዳችን በተቋማዊ የሪፎርም ስራዎቻችን በተገኘ ውጤት  መነሻ  ምክር ቤታችን ራሱን በስኬታማነት አደራጅቶና  በጥሩ የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅም ላይ ሆኖ የተቀመጠ እቅድ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።ስለሆነም፤   ይህንን የተገኘ ውጤት ለማስቀጠል አባላትን በማደራጀት እና የበለጠ በማጠናከር  በአገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ገበያዎች ዉስጥ ተወዳዳሪ የሆነ የግል ዘርፍ በሚጠናከርበት ስትራተጂካዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሰሩ ማስቻል የበጀት አመቱ ቁልፍ ስራችን ይሆናል።

በተያያዘም፤  የንግዱን ማህበረሰብ ጊዜው የሚጠይቀው እውቀት እና ክህሎት ሊያጎለብቱ የሚችሉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ዉጤታማ ንግድ በአገሪቱ እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መከወን በዕቅድ ውስጥ ተካትቷል።

በተጨማሪም፤ መላው የንግዱ ማኅበረሰብ በኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነት(CSR) የአሰራሮች ማዕቀፍ  የመንግስት ኢኒሼቲቭ በሆኑ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎችና በሰላም ግንባታ ዙሪያ የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት  የሚያስችለው ዕቅድ ቀርፀናል ::

በሌላም  በኩል፤  የምክር ቤታችንን ባለ 23 ወለል ህንፃ ግንባታ የምናስጀምር ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅም ምክር ቤታችን  በቴክኖሎጂና በዲጅታላይዜሽን አሰራሮች ለማዘመን ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

በዚህ አጋጣሚም ለ2018 ዕቅድ ስኬታማነት ፤ ለምክር ቤታችን የዴሬክተሮች ቦርድ አባላት፤ የምክር ቤቱ የስራ ኃላፊዎችና
ባለሙያዎች እንዲሁም አባል ምክር ቤቶች፣ የባለድርሻ አካላት እና አጋሮቻችን  ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia