Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 08, 2026 .

አቶ ጀማል አህመድ የኢትዮጵያ አገር አቀፍ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት፣ አቶ በላይነህ ክንዴ ምክትል ፕሬዚደንት ሆናችሁ በመመረጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ :- ሰብስብ አባፊራ

–

የኢትዮጵያ አገር አቀፍ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባካሄደው ምርጫ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት እንዲሁም አቶ በላይነህ ክንዴ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው በመመረጣቸው በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፥ በመላው አባል ምክር ቤቶቻችን እንዲሁም በራሴ ስም እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ምክር ቤታችን ፤  የአምራች ዘርፋ በአገራችን የኢኮኖሚ ልማት ካለው ቁልፍ ሚና አንፃር እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ፣ ተኪ ምርቶችን ከማምረት እንዲሁም በወጪ ንግድ ላይ ካለው አገራዊ ሚና አንፃር የሚጠበቅበትን ተልዕኮ ሁሉ እንዲወጣ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በጋራና በትብብር እንደምንሰራ አረጋግጣለሁ።

የቀድሞው የቦርድ አባላት ለአመታት ደከመን ሰለቸን ሳትሉ ዉድ ጊዜያችሁን ፣ ገንዘባችሁንና እውቀታችሁን ሰውታችሁ ለዘርፉ ላደረጋችሁት አስተዋፅኦ ክብርና ምስጋና ይገባችሁአል እላለሁ ::

በዚህ አጋጣሚ፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 341/95 የተሰጡትን ተልእኮዎች ለማሳካት እያከናወንናቸው ያሉ ተቋማዊ የለውጥ ስራዎች  በላቀ መልኩ ፍሬያማ እንዲሆኑ ፤ የኢትዮጵያ አገር አቀፍ የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን ጨምሮ ሁሉም አባል ምክር ቤቶቻችን በተጠናከረና በጋራ አገራዊ የትብብር መንፈስ እንድንሰራ አደራ እላለው።

በመጨረሻም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለው!

ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት  ፕሬዚደንት

Hoji Gaggeessaa Ol’aanaan  Garee Invastimantii Miidirook, Obbo Jamaal Ahimad Pireezidaantii Mana Maree Waldaalee Sektera Itoophiyaa ta’anii yoo filataman, Abbaan Qabeenyaa beekamaan Obbo Balaayineh Kindee ammoo itta aanaa Pireezidaantii ta’uun filatamaniiru.
Pireezidaantiin Mana Maree Daldalaafi Waldaale Sektera Itoophiyaa Obbo Sabsib Abbaafiraa, hoggantootaa haarawaa filatamaniif ergaaa baga gammaddanii dabarsuun, hoggantoota duraanii yeroofi beekumsa isaanii gumaachuun yeroo dheeraaf tajaajilaa turanii yeroo turtii isaanii xumuranii aangoo  dabarsanii kennanis galateeffataniru.
Manni Maree Daldalaafi Waldaalee Sekteraa sdarkaadhaan jiran Aangoofi Itti gaafatamummaa, akkasumas ergama Labsii Lakk 341/1995n  itti kennaman milkeessuuf  riifoormiiwwan sadarkaa biyyaalessaatti jalqabaman  daran cimsuun hojii bu’a qabeessa akka hojjetanis Obbo Sabsib dhaamsa dabarsaniiru.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia