Read more

Nov 26, 2026 .

አዜቴክስ ሰርቪስስ WLL ኩባንያ ተወካዮች ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር ተወያዩ።

 

በውሃ አመራረትና አስተዳደር፣ በታዳሽ ኃይል፣ በኤሌክትሪክና ኃይል ምህንድስና፣ በሕክምና ተቋማት ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች ላይ የሚሠራው፤ አዜቴክስ ሰርቪስስ WLL ኩባንያ ተወካዮች ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር ተወያዩ።

በውይይቱም የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀኃፊ ወይዘሮ ሄለን ረታ የተገኙ ሲሆን በማቀዝቀዣእና በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች ላይ የሚሠሩ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችም ተሳትፈዋል።

መቀመጫውን ባህሬን ያደረገው ኩባንያው ከኢትዮጵያ አቻ ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመሥራት እንደሚፈልግ በተለይም በማቀዝቀዣ ሰንሰለት አስተዳደር፣ በፀሐይ ኃይል፣ በእሳት ደህንነትና በሌሎች ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋፋት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።
ኩባንያው ከጥር 26 -30/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው ኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ እንዲሳተፍም ጥሪ ቀርቦለታል።

Representatives of Bahrain-based Azetex Services WLL held discussions with ECCSA on potential areas of business cooperation.The meeting, attended by ECCSA Deputy Secretary General Mrs. Helen Retta and representatives of Ethiopian companies, explored partnership opportunities in cold chain management, solar energy, fire safety, water management, power engineering and healthcare waste management.

Azetex Services expressed its interest in collaborating with Ethiopian companies and was invited to participate in the 16th Ethio-Chamber International Trade Fair, scheduled for February 3–7, 2027, in Addis Ababa.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia