ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፡ በተግባር የታነጸበት ስራ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፡ በተግባር የታነጸበት ስራ
ዛሬ በሞጆ ተገኝተን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና የሚጫወተውንና በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፍያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስመርቀናል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ጣቢያዎችና ዘመናዊ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን፣ የደረቅ ብትን ጭነቶችን በሀገር ውስጥ እንድናሽግ ማስቻሉ፣ የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ ባለፈ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። የማዕከሉን የአሰራር ፍጥነት ለማሳደግ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተተከለው የባቡር ላይ ክሬን ከባቡር መስመር የሚደረገውን የኮንቴነር ዝውውር በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።
ሙሉ አሰራሩ በዘመናዊ ዲጂታል መሰረተ ልማት የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተገልጋዮች ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎትን ያሳልጣል። ይህ ማዕከል ከኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ባሻገር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን የሚያስተሳስረው የ‘ደሱ’ ኮሪደር አካል ሲሆን፤ ይህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ደረጃ ላይ ያላትን ስፍራ የሚያሻሽልና የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስራችንን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ ድል ነው።

𝗘𝗧𝗛𝗜𝗢𝗣𝗜𝗔’𝗦 𝗣𝗔𝗧𝗛 𝗧𝗢 𝗔𝗳𝗖𝗙𝗧𝗔, 𝗥𝗢𝗢𝗧𝗘𝗗 𝗜𝗡 𝗔𝗖𝗧𝗜𝗢𝗡
Today in Mojo, we inaugurated the first phase of the modern logistics center expansion, a 60-hectare hub set to play a major role in making the #AfCFTA a success for Ethiopia and the continent. With terminals and warehouses capable of handling up to a million 20ft containers a year, the center allows dry bulk cargo to be packaged domestically, saving foreign currency and opening up broad employment opportunities for our citizens. Its efficiency is powered by the country’s first-ever Rail-Mounted Gantry crane, moving containers from the rail line at high speed.
Built on a fully digital infrastructure, the center guarantees fast, reliable service. Beyond the Ethio-Djibouti line, it forms part of the DESSU Corridor linking Ethiopia, South Sudan, and Uganda, a milestone that strengthens our place in the global logistics sector and opens a new chapter in regional economic integration.
#EthiopiaDelivers
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
