Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 10, 2026 .

ዶ/ር አይናለም አባይነህ ከስሪላንካ የንግድ ተቋማትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በኮሎምቦ ውይይቶችን አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አይናለም አባይነህ ከስሪላንካ የንግድ ተቋማትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በኮሎምቦ ውይይቶችን አካሂደዋል።

ውይይቶቹም በኢትዮጵያና በስሪላንካ መካከል የግሉ ዘርፍ ትብብርን ማጠናከር ላይ ያተኮሩ ነበሩ።

የሁለትዮሽ የጋራ የንግድ ምክር ቤት ለማቋቋም፣ የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ለመፈራረም፣ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ማኅበረሰብ በSri Lanka Expo 2027 እንዲሳተፍ ለማመቻቸት በውይይቶቹ ትኩረት ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ልዑካን በተጨማሪም በከበሩ ማዕድናት፣ በማዕድን ማውጫና በኮኮናት ዘርፎች ከሚሰሩ የስሪላንካ ኩባንያዎች ጋር የንግድ-ለ-ንግድ ውይይቶችን አካሂዷል። ውይይቶቹም አዳዲስ የንግድ አጋርነቶችን፣ የገበያ ትስስሮችንና የአቅርቦት ሰንሰለት ትብብርን ለማስፋት ያለውን ዕድል ያጠናክራል።
❇️❇️❇️❇️❇️

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Vice President Dr. Aynalem Abayneh held high-level talks with Sri Lankan trade institutions and private-sector representatives to strengthen Ethiopia–Sri Lanka business relations.
Discussions focused on establishing a bilateral business council, signing an MoU, promoting trade and investment, and enabling Ethiopian businesses to participate in Sri Lanka Expo 2027.
The delegation also engaged Sri Lankan companies in the gemstone, mining and coconut sectors, exploring new commercial partnerships, market opportunities and supply-chain cooperation.

For more info:
https://www.mfa.gov.lk/en/news/ethiopian-chamber-vice-president-engages-high-level-trade-and-business-discussions-sri-lanka

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia