Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 29, 2025 .

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) ሙሉ አባል የመሆን ህልሟን እውን ለማድረግ የድርድሩ ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) ሙሉ አባል የመሆን ህልሟን እውን ለማድረግ ባደረገችው ጽናት የተሞላበት ጉዞ እና የድርድሩ ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች።

ኢትዮጵያ ከሃያ ዓመታት በላይ በዘለቀው የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር አገሪቱ ከዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ጋር ያላትን ትስስር ለማጠናከር የያዘችውን  ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ ሲሆን በተለይም በዚህ አንድ ዓመትጊዜ ውስጥ የተካሄደው ድርድርና በሂደቱ የተደረሰበት ደረጃ አስደማሚ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር እና የኢትዮጰዯያ ዋና ተደራዳሪ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO)  እ.ኤ.አ ጥር 1/1948 የተመሰረተውን የንግድ ታሪፍ እና አጠቃላይ የንግድ ስምምነት (GATT)  ተልዕኮ በመውረስና በማስፋት እ.ኤ.አ ጥር 1/1995 የተመሰረተ ትልቅ ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስር ማእቀፍ ነው፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት ሲመሰረት በ30 አባል ሀገራት ተጀምሮ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ 166 አባል ሀገራትን አካቷል።  ይህ ድርጅት ዓለም አቀፍ የንግድ ደንቦችን በማውጣት የዓለምን 98% ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንግድ ሥርዓት ፈጥሯል።

ኢትዮጵያም WTO ከተመሰረተበት 1995 ጀምሮ የአባልነት ድርድሩን ሂደት ጀምራለች። በድርድር ሂደቱም የብዙ ወገን ድርድር እና የሁለትዮሽ ድርድሮችን እያካሄደች ሲሆን በተለይም ከ5ኛው የስራ ላይ ቡድን ስብሰባ ወዲህ በጣም ፈጣንና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት ድርድር መካሄዱን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ጀኔቭ ላይ በተካሄደው 6ኛ የስራ ላይ ቡድን ጉባኤ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ካቀረበች ከ20 ዓመታት በላይ በፈጀው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ የተመዘገበበት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ካሳሁን ይህ እምርታ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለድርጅቱ አባልነት መቃረቧን የሚያመለክት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ስድስተኛው የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባ የረጅም ጊዜ ድርድሩን ወደ ፍጻሜ ለማድረስ ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ አሁን ላይ የደረሰችበት ሂደት የሀገሪቱን የንግድ የወደፊት ተስፋ የሚያመላክት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ለWTO አባልነት ያደረገችው ጉዞ ተግዳሮቶች የነበሩበት ቢሆንም አገሪቱ ዓለም አቀፍ የንግድ ደንቦችን ለማክበርና ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ያላትን ጠንካራ ፍላጎት የሚያሳይ ነው። (ን/ቀ/ት/ሚ)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia